ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን የኦስካር የክብር ተሸላሚ ሆነ

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን የኦስካር የክብር ተሸላሚ ሆነ

ታዋቂው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን የኦስካር የክብር ተሸላሚ ሆነ

በማርሻል አርት ፊልሞቹ በርካቶች ዘንድ ታዋቂነትን ያተረፈው ቻይናዊው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን የኦስካር የክብር ተሸላሚ ሆኗል።

የፊልም ደራሲ፣ ዳይሬክተር፣ ተዋናይ እና ማርሻል አርቲስት ጃኪ ቻን ለዚህ ክብር ሊበቃ የቻለው በፊልም ኢንደስትሩው ለተቀዳጀው ከፍተኛ ስኬት ነው ተብሏል።

የ62 ዓመቱ ቻይናዊ ጃኪ ቻን ፊልም መስራት የጀመረው በሚኖርባት ሆንግ ኮንግ ከተማ ነው።

ጃኪ ቻን የ6 ዓመት ታዳጊ እያለ የመጀመሪያ ፊልሙን የተቀረፀ ሲሆን፥ በፊልም ኢንደስትሪው ውስጥ ለ56 ዓመታት እያገለገለ ይገኛል።

እስካሁንም ከ200 በላይ ፊልሞች ላይ እንደተወነ ጃኪ ቻን ይናገራል።

ጃኪ ቻን በተለይም “Rumble in the Bronx፣ Rush Hour እና Kung Fu Panda በሚለው የአኒሜሽን ፊልሞቹ ከዓለም ዙሪያ በርካታ አድናቆቶች ጎርፈውለታል።

 

jc_2.jpg

 

የአሜሪካው የፊልም አካዳሚ ከጃኪ ቻን በተጨማሪ በፊልም ኢንደስትሪ ውስጥ ስኬታማ የሆኑ ሶስት ሰዎች ተሸላሚ እንዲሆኑ መርጧል።

እነዚህም የፊልም ኤዲተር አኔ ኮስተስ፣ የፊልም ዳይሬክተር ላይን ስታልማስተር እና የዶክመንተሪ ፎልሞችን በመስራት ዝናን ያተረፈው ፍሬደሪክ ዋይዝማን ናቸው።

jakie.jpg

የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ቼርይል ቦን፥ አራቱም የፊልም ባለሙያዎች ለዚህ ክብር ሊበቁ የቻሉት በዘርፉ ላስመዘገቡት ስኬት እና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው ብሏል።

ጃኪ ቻን የኦስካር የክብር ተሸላሚ መሆኑን ተከትሎ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፥ ለዚህ ክብር በመብቃቴ ኩራት እና ክብር ይሰማኛል ብሏል።

ለዚህ ክብር የበቃው ብቸኛው ቻይናዊ የፊልም ተዋናይ ነኝ ሲልም ራሱን አሞጋግሷል።

ጃኪ ቻን’ን ጨምሮ ለኦስካር የክብር ሽልማት የታጩት የፊልም ባለሙያዎቹ የፊታችን ህዳር ወር ላይ ሽልማታቸውን እንደሚቀበሉም ታውቋል።

ምንጭ፦ www.bbc.com/news/entertainment