የየም ብሄረሰቦች ባህላዊ አሰተዳደር

የየም ብሄረሰቦች ባህላዊ አሰተዳደር

 

 

 

 

 

የተለያዩ የታሪክ መጽሀፍ የብሔረሰብ ታሪክ አዋቂዎች መረጃ እንደሚያ መለክተዉ የየም ብሄረሰቦች የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ የሆነ አደረጃጀቶች ተከትሎ  የሚመራበት የአስተዳደር ስርአትና የስልጣኔ ተዋረዶች እንደነበሩት ያመለክታሉ ዘመናዊ አስተዳደር ጽንሰ ሀሳብ የተከተለ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መዋቅሮችንማ ይከተል ነበር፡፡ የየም ብሔረሰብ በደቡብ ማዕራብ  ኢትዮጵያ ብቸኛዉ ጠንካራ መንግስት እንደነበረና ታላቋ ኢናሪያ መንግስት ገዥ እንደነበር የጹፍ እና የብሔረሰብ ታሪክ አዋቂ አባቶች መረጃ ይጠቁማሉ ይህ መንግስት የራሱ የሆነ ንጉስና በቅብአ ንግስና ሌሎችም ንጉሶች በማንገስ የደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች  በኮንፍድሬሽን ያስተዳደር ነበር፡፡

 

አንጋሪ ቤተ መንግስት ይባላል፡፡ የብኄረሰቡ ነገስታት መቀመጫ ነዉ፡፡ ይህ ቤተ መንግስት እስከ መጨረሻዉ ንጉስ ንጉስ ጌራኖ ቦጊቦ (ፊትዉራሪ ገ/መድህን አስከ 1948 ዓ.ም ድረስ) የሶስት ጎሳዎችን ስረወ መንግስት አስተዳድሯል፡፡ እነሱም የጋማ፤ የጌሜሎ እና የሞዋ ጎሳዎች ስርወ መንግስት አስተዳድሮዋል፡፡ እነሱም የጋማ ፤ የጌማሎ እና የሞዋ  ጎሳዎች ስረወ መንግስታት እስተዳድሯል፡፡እነሱም የጋማ፤ የጌሜሎ እና የሞዋ ጎሳዎች ስረወ መንግስት ሲሆን የመጨረሻዉ ስርወ መንግስት ከ 13ኛዉ ክ/ዘመን ጀምሮ አስራ አንድ የሚሆኑ የጎሳዉ ነገስታት ህብረተ ሰቡን አስተዳድሮዋል፡፡ እነዚህ ነገስታት ባልወለድ፤አዛግኖ ፤ ቶኪኖ፤ስልባቡኖ ማዉዳድኖ፤ኮኬና፤ኖዲኖ፤ዘርዳዲኖ፤ዲጋመረኖ፤ኢዳሎኖ፤ ጉሳሲኖ (ቦጊቦኖ) በመባል ይታወቃሉ፡፡

የየም ንጉስ ‹‹ታቶ›› የሚባል የንግስና ሰያሜ የነበረዉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የብሄረሰብ አባላት ለንጉስ ባላቸዉ ልዩ ክብርና ጥንቃቄ የተነሳ አምኖ (ከፍታችን) እና ኮምኒ (አይናችን) የሚባሉ ስያሚዎች በተጨማሪነት ይሰጣሉ፡፡

 

‹‹ታቶ›› በፖለቲካዊና ሀይማኖታዊ ገዳዮችን በበላይነት የሚያስተዳደር ሲሆን በስሩም የተለያዩ አደረጃጀቶችን አቅፎ የያዘ ነዉ፡፡ ከታቶዉ ጋር ቀጥተኛ የሆነዉ ተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸዉ ስምምነት አካላት አሉ፡፡

 

የመጀመሪያዉ ‹አስቴስር› ሲሆን የንጉስ ከፍተኛ የስልጣን ባለቤቶች ናቸዉ እነዚህ አባላት በህዝብ የሚመረጡ ሲሆን ከታላላቅ እና ከታናናሽ ጎሳዎች የተመረጡ አስራ ሁለት አባላት የያዘ ነዉ፡፡ ይህም አሁን ካለዉ የሚኒስቶች ም/ቤ ት ጋር ሊመሳሰል  ይችላል፡፡ ሁለተኛዉ ‹ናንቴሴር› ይባላል፡፡ ከሁሉም ጎሳዎች የተወጣጡና አባላት የያዙ ሲሆን ከጎሳ አባላቶች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለአስቴሰሮች በማቅረብ ምላሹን ለህዝብ የሚያደርሱ አባላት ስብስብ ነዉ፡፡ ከዛሬዉ የተወካዮች ም/ቤት ጋር  ሊመሳሰል ይችላል፡፡

 

ሶስተኛዉ ጦርነትና የመከላከያ ጉዳዮች በተመለከተ ንጉስን የሚያማክሩ አባላትን ያቀፈዉ አካል  ‹ሜንቴሴር› ከዛሬዉ የመከላከያ  ሚኒስቴር ጋር ሊመሳሰል የመከላከያ ሚኒስቴር ጋር ሊመሳሰል ይችላል፡፡ አራተኞችና ‹ፋንቴሰር በመባል የሚታወቁት አባላት ደግሞ በሀብት እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ  ንጉስን የሚያማክሩ አካሎች ናቸዉ፡፡

 

አምስተኛዉ በንጉስ ግዛት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በመንተንበይ ለንጉስ የሚያቀርበዉና የሚያማክረዉ አካል ‹ፋራቴሰር› ሲባል ህግና ደንብን የሚያመነጭ አካላት የያዘዉ ስድስተኛዉ መማክርት ደግሞ ‹ቱምቴሰር› በመባል ይጠራል፡፡

 

የፍትፍ  ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ንጉሱን የሚያማክሩ አካላት ‹ፊላቴሰር› ሲባሉ የንጉስ ልዩ አማካሪ በንጉስ ላይ ድንገተኛ ችግር ሲደርስ ሌላ ንጉስ እስኪተካ ድረስ ተወክሎ የሚመራዉ ‹ዋሶ› ነዉ፡፡ በዋናነት አስቴሰሮችን የሚመራ ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔ ሃሳብ ለንጉስ አቅርቦ ያጸድቃል፡፡

 

ከላይ የተጠቀሱ የንጉሳዊ  አስተዳደር አካላት በተጨማሪ በብሄረሰብ ዘንዱ ህዝቡን በቅርበት የሚያስተዳድር አካላትም የተለያዩ ስልጣን ደረጃ ተሰጥቷቸዋል የሚመሩበት ሁኔታ ነበር፡፡ እነሱም ኤራሾ፤ ጋኛ፤ናስጋኛ፤ጉርሙ እና ዎሲ ይባላሉ፡፡

 

ኤራሾ ከአስቴሰር ቀጥሎ የስልጣን ባለቤት ሲሆን የክፍለ ግዛት ገዥዎች ስልጣ ማለት ነዉ፡፡ በስራቸዉ ያሉ የተለያዩ አካላት ይመራሉ፡፡ ጋኛ ከኤራሾ ከጥሎ ያለ የአካባቢ ገዥዎች ስልጣን ማለት ነዉ በስራቸዉ ያሉ የተለያዩ አካላት ይመራል፡፡ ጋኛ ከኤራሾ ቀጥሎ ያለ የአካባቢ ገዚዎችን ስልጣን ሲሆን ተጠሪነቱ ለጋኛ ነዉ፡፡ ጉርሙ የአካባቢ ገኛዎችን ከክፍል ግዛቱ ኤራሾዎች ጋር የሚያገናኝ እና አማካሪ ነዉ፡፡ ዎሲ የየአካባቢዉ ገዚዎች መልዕክተኛ (ዎሲ ) ነዉ፡፡

 

የየም ብሄረሰብ የማህበራዊ አስተዳደር ጉዳዮችና ስርዓቱን የሚያስፈጹሙ የጎሳዎች ዉክልና በጠበቀ የሚሰየሙ አበላትም ነበሩተ፡፡

 

 

እነሱም ጂጋ፤ቶጎ፤ለጋ፤ረጂ፤እና ሺኒ ይባላሉ፡፡ ሺኒ የተወሰኑ የሰፈሩ አባዎራዎችን ያቀፈ የጎጥ አለቃ ነዉ ከሺኖዎች አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ለረጂ ያስተላልፋል፡፡ረጂዎችም ከሺኒ የአመራር እርከን በላይ የሆኑ  ጉዳዮችን ተከታትሎ ዳኝነት ይሰጣሉ፡፡ ለጋ በረጂ ደረጃ ያልተፈቱ ችግሮች ወይም ጉዳዮች ሲኖሩ መፍትሄ የሚሰጡ  አካላት ናቸዉ፡፡ ቶጎ ከለጋዎች  አቅም በላይ የሚሆኑ ጉዳዮች ሲቀርብ ተመልክቶ ውሳኔ የሚያስገኝ አካል ነዉ፡፡ በሌላ በኩል በቡሄረሰብ ቋንቋ ባለስልጣን ‹ጋኛ› ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የተለያዩ ወቅታዊ ተግባራትን የሚያከናዉኑ ቡድኖች የሚመሩ አካላት በዚያ የስልጠና ስም ይጠራሉ ለምሳሌ የየር  ጋኛ (የኤደን ቡድን መሪ፤ሜን ጋኛ (የጦር ኢላማ  መሪ) በመባል ይጠራሉ፡፡

 

የቻሎት ባህላዊ ዳኝነት

 

ቻሎ ከየም ልዩ ወረዳ ርዕስ  ከተማ ፎቶ በስተደበብ አቅጣጫ በ11.8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ የባህላዊ ዳኝነት የሚፈጸምበት ስፍራ ነዉ፡፡ ከልዩ ወረዳዉ ከተማ ፎቶ ወደ ቶባ ገጠር ከተማ ሴኬድ የቦር ተራራ ይገኛል ይህን ዉብ ስፍራ አልፈን አምባ ምድር ላይ ብቅ ስንል ቻሎን እናገኛለን በየስሙ አዋሾ እና ሾሻር አልማም ቀበሌያት መካከል፡፡

 

የቻሎ ባህላዊ ዳኝነት ስነስርአት የሚፈጸመዉ በአመት ሀለት ግዜ ሲሆን አንደኛዉ ከመስከረም 17 የመስቀል ዳመራ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት እና ከሚያዚያ 27-28 ባሉ ሁለት ቀናት ይፈጸማል፡፡ መስከረም 14 ቀን ሲደርስ ቻሎ ቱና (የቻሎ አደባባይ) በሚባለዉ የመስቀል መጨፈሪያ ቦታ ላይ ኮን ጋኛ፤ሜን ጋኛ እና አዉሎን ጋኛ የሚባሉት ሶስት ዳኞች ማር በኮባ ይዘዉ በመሄድ በአሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሁም በመጸለይ በአሉ እንዲጀም ያደርጋሉ፡፡ ይህ ሁኔታም ‹‹ካሚኬሳ›› ይባላል፡፡ ካማ ማለት ማር ሲሆን ኬሳ ማለት ደግሞ ከባሉ በፊት ማለት ነዉ፡፡

 

የቻሎ ባህላዊ ዳኝነት ከአንድ ጎሳ የተመረጡ ሶስት ዳኞች  አሉት፡፡ የባህላዊ ዳኝነቱ የፍርድ አሰጣጡ በተገቢዉ መንገድ መካሄዱን የሚቆጣጠሩ ከተለያዩ ጎሳዎች የተወጣጡ አስራ ሁለት የሚደርሱ ስርአት አስከባሪ ሽማግሌዎች ጋር በመሆንም የፍርድ አሰጣጥ ስርአት ይከናወናል፡፡ እነዚህ ሽማግሌዎች የስራ ድርሻ ባህዊ ዳኞች ፍርዱን በአባቶች ወግና ልምድ መሰረት መፈጸም አለመፈጸማቸዉ መታዘቡን የችሎት ሂደት ሲወርድ ሲዋረድ በመጣዉ ባህላዊ ስርአት መሰረት መከናወን አለመከናወኑን መከታተል ነዉ፡፡

 

የዳኝነቱ ስርአት ሂደት

የቻሎ ባህላዊ ዳኝነት ሂደት በየአመቱ መስከረም 17 ቀን በቻሎ ካንቻ ወረዳ የመስቀል በአል መፈጸሚያ ቦታ /በዳመራ  የሚጀምር ነዉ፡፡ በመስከረም ሚያዚያ የችሎት ወቅቶች ፍትህ ያገኙ አመልካቾች ለፍርድ የሚያስፈጸም ካበረከቱት ገንዘብ ውስጥ ተወስዶ ፍየል ይገዛል፤ በቻሎ ካንቻ ፍየሉ ይታረዳል፡፡

 

ሶስቱ ዳኞች  ታዛቢ ሽማግሌዎች ከተሰየመ በኋላ አቤቱ በቀረበበት ቀን ይቆረጣል መልእክቱ ለተከሳሽ የሚላከዉ ቃል ነዉ፡፡ ወንጀል ፈጻሚዉ ሽማግሌዎች ወንጀሉን ሲመረምረዉ ራሱን የማጋለጥ ፍቃደኛ  ሳይሆን ቢቀር ወይም መልዕክት ደርሶት በቂ ግዜ እያለዉ እስከ መስከረም 23 መቅረብ ካልቻለ የእርግማን ስርዐቱ ይፈጸማል፡፡

 

እርግማኑ የሚፈጽሙት ‹‹ቦጊኛ›› ቡድን የጌሎና ናማ በክብረ በአሉ ወቀት በየቤቱ መዘዋወር ቤት የሚያፈራዉን ምግብና መጠጥ በመመገብና በመጣጣት አናታቸዉንና ጋሻቸዉን ቂቤ ይቀባሉ፡፡ ከዘጠኝ ሰዐት በኋላ ወደቻሎ ካንቻ ሲደርሱ በፈረሶቻቸዉ እያሶማሶሙ የተለያዩ ትሪቶችን በማሳየት ከበአሉ ታዳሚዎች ጋር ይቀላቀላሉ፡፡ መስከረም 23 የመስቀል (ሄቦ) በዓል ማጠናቀቂያ ስለሆነ ከህዝቡ ጋር በአሉን በማድመቅ ይጫወታሉ፡፡

 

ማምሻዉን ከ12 ሰኣት በኋላ ከዳኞቹ አቅም በላይ ሆኖ ለእርግማን የበቃ ጥፋተኛ ካለ በመርገሚያ ቦታ ሄደዉ የእርግማን ስርአቱን ይፈጸማል፡፡ የመስከረም 23 የዳኝነት ስርአት መቀበያ ይሆናል በእለቱ የተለያዩ ዳኝነት ስርአት ማብቂያ ይሆናል፡፡ በእለቱ በተለያየ ምክንያቶች ያለታዩ ጉዳዮች ወደ ሚያዚያ 27-28 ይተላለፋል፡፡

 

የቻሎ ማህበራዊ ፋይዳ በብሄረሰብ አባላት መካከል ሰላምን ማስፈን፤አንድነትን ማስጠበቅ፤ የዳኝነት ህልዉና ማስቀጠል ነዉ በስዉር ከእይታ ዉጪ የተፈጸመ ወንጀሎች ፍትሀዊ ከሆነ መንገድ መታየታቸዉ ህብረተሰብ በራሱ ባህላዊ ዳኝነት ላይ እምነት እንዲያሳድር ጉልበተኛዉ እንዳይመካ እና አቅም አቅም ያጣዉ እንዳይሰጋ ያደርጋል፡፡ ሌላዉ ባህላዊ ፋይዳ ስነ ስርዐቱ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና ቀጣይነት ያለዉ መሆኑ ነዉ፡፡

 

በአጠቃላይ የቻሎ ባህላዊ ዳኝነት እንደ ክህደት፤ ደፈጣ፤ዘረፋ፤ድብደባ፤ቤት ማቃጠል፤ስዉር ግድያ እና ወዘተ የመሳሰሉ ተጨባጭ መረጃ  የሌላቸዉን ወንጀሎች  የሚጋለጡ ሚና ከፍተኛ ነዉ፡፡ስዉር ድርጊቶችና ወንጀሎች የሚጋለጡ ሚና ከፍተኛ ነዉ፡፡ ስዉር ድርጊቶች  ወንጀሎች በቻሎ ባህላዊ ዳኝነት ያለወጪ ፈጣን ፍትህ ማግኘታቸዉ የማህረሰቡን ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ ያለዉ ፋይዳ የላቀ በመሆኑ ሊበረታታና ሊደገፍ ይገባል፡፡

 

ምንጭ፡- ማህደረ ደቡብ