የማር ጥቅም ከህክምና አንፃር

 

የማር ጥቅም ከህክምና አንፃር

 

 

Image result for honey

 

ማር ስኳር እስከተገኝበት 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫ በመሆን ያገለግል ነበር የአሰራር ሂደቱ በጣም አስደናቂ ከመሆኑም ባሻገር በብዙ ሰዎች ተወዳጅና ተመራጭ የምግብ ዓይነት ነው። በፍሩክቶስ(fructose) ይዘቱ በጣም የበለፀገ ስለሆነ ብዙ የህክምና ጥቅሞች አሉት እነሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ።

 

1. የካንሰርና የልብ ህመም ይከላከላል

የተፈጥሮ ማር ፍላቮንድና አንቲ ኦክሲዳንት(antioxidant) በውስጡ ይዟል እነዚህ ነገሮች በካንሰርና የልብ ህመም የመጠቃት እድልን ይቀንሳሉ።

 

2. የአንጀት መቁሰልን ይከላከላል

ማር አንጀታችን በባክቴሪያ ሲጠቃና በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይቆስል ይከላከላል።

 

3. ማር ፀረ ባክቴሪያና ፀረ ፈንገስ ነው

በኒውዝላንድ ዋይካቶ ዩኒቨርስቲ የማር ምርምር ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ፒተር ሞላን ሪፓርት እንደሚያሳየው ማር ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ አለው ምክንያቱም ንብ ማር ውስጥ ሀይድሮጂን ፐር ኦክሳይድ (hydrogen per oxide) የተባለ ኢንዛይም ትጨምርበታለች።

 

4. የአትሌቶችን ብቃት ይጨምራል

በድሮ ጊዜ የሚገኙ አትሌቶች ብቃታቸውን ለመጨመር ማርን ይጠቀሙ ነበር ይህ ተግባር በአሁኑ ዘመናዊ አትሌቲክስ የተረጋገጠ ሲሆን የግላይኮጂን መጠን በማመዛዘን ጉልበት እንዲያገኙ ያደርጋል።

 

5. ማር ሳል እና የጉሮሮ መቆጣትን ይቀንሳል

ቀይ ማር ለሳል በጣም ጠቃሚ ነው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በ110 ህፃናት ላይ በተደረገው ጥናት መሰረት እኩል መጠን ያላቸው ቀይ ማር እና ዴትሮሜትሮፌን(detromethorphan) ተመሳሳይ የሆነ በምሽት ከሚነሳ ሳል እኩል የማስታገስ አቅም ያላቸው ሲሆን ሰላማዊ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርጋል።

 

6. አምስቱ ንጥረ ነገሮችን ያመጣጥናል

ማር እይታ እና የክብደት መቀነስን ያሻሽላል። ስንፈተ ወሲብን እና ቅድመ ዘር ፍሰትን ይፈውሳል እንዲሁም ሽንት መስተጓጐልን፣ የመተንፈሻ አካላት ስርዓትን፣ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽን መከላከል ይችላል።

 

7. ማር በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቆጣጠራል

ማር ምንም እንኳን አነስተኛ መጠን ያለው ስኳር ቢኖረውም ሰው ሰራሽ ከሆነው ስኳር ጋር ግን ተመሳሳይ አይደለም። የፍሩክቶስ ና ግሉኮስ ጥሩ የደም የስኳር መጠንን ቅንጅት ይቆጣጠራል። በተጨማሪም አንዳንድ የማር አይነቶች አነስተኛ/ዝቅተኛ የስኳር መጠን ስላላቸው የደም የስኳር መጠን እንዳይዋዥቅ ያደርገዋል።

 

8. ማር የሰውነት ቁስለትንና ቃጠሎን ይፈውሳል

ማርን በውጨኛው የሰውነት ክፍላችን ላይ ከሲልቨር ሰልፋዲያዚን(silver sulfadiazine) አብረን መጠቀም ፍቱን መድሀኒት ነው። በማር ውስጥ ያሉት ቀላል ስኳሮችና የፀረ ባክቴሪያ ባህሪው ቁስል ቶሎ እንዲድን ያደርገዋል።

 

9. ስነ ህይወታዊ ባህረ

አንዳንድ የማር አይነቶች የተለመድ የማይጓድ ባክቴሪያዎችን ይዘዋል እነሱም 6 የሚሆኑ የላክቶ ባሲላይ ዝርያዎችና 4 የቢፊዶ ባክቴሪያ ናቸው በመሆኑም ማር ዘርፈ ብዙ የሆነ ህመምን የመፈወስ ጥበብ እና ባህሪያት አካቷል።

 

10. ለቆዳ ውበት

የማር የፀረ ባክቴሪያ በዋነኛነት ለቆዳ ተስማሚ እና ጠቃሚ ነው። ከሌሎች ጋርም በመሆን ቆዳን የማለስለስና የማርጠብ ከፍተኛ አቅም አለው።

 

ትኩረት የሚሹ የማር መልዕክቶች

ጠቆር ያለ ጠይም ማር አንቲ ኦክሲዳንት ባህሪ አለው

ከአንድ አፀዋት ብቻ የሚሰራ ማር አነስተኛ የግላይሴሚያ ኢንዴክስ(glycemia index) አላቸው

 

በመጨረኛም

እርስዎ የኢንሱሊን መቆጣጠሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት መድሀኒት የሚወስድ ከሆነ፣ ከመጠን ያለፈ የኮሌስትሮል መጠን በሰውነትዎ ካለ፣ የስኳር በሽተኛ ከሆኑና ከአቅም በላይ ውፍረት ከኖረብዎትጣፋጭ ነገሮችን ማለትም ማር እና ስኳር የመሰሉ ነገሮችን አብዝቶ ከመውሰድ ራስዎን ይቆጥቡ።

ስለሆነም የማርን ጠቀሜታ በአግባቡ ለማጣጣም ንጽህናው የተጠበቀና ተፈጥሮአዊ ማርን ብቻ በመጠቀም በማር ውስጥ የሚገኝውን የቫይታሚን፣ ኢንዛይምና ሌሎች ንጥረ ነገሮችና ሚነራሎችን ማግኝት ይችላሉ።

ምንጭ፦http://sodere.com/group

 

  

Related Topics