የእንቁላል ቅርፊትን መጠቀም የምንችልባቸው አስገራሚ መንገዶች

የእንቁላል ቅርፊትን መጠቀም የምንችልባቸው አስገራሚ መንገዶች

 

 

 

የእንቁላል ቅርፊት በተለይ በሀገራችን በተለምዶ ወደ ቆሻሻ ወይ ወደ ውጪ ከመወርወርና ከመጣል ውጪ ሌላ ጥቅም የለውም።

ግን ዝሬ የእንቁላል ቅርፊት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉትና ከነሱም ለኛ ይጠቅመናል የምንለውን እናያለን።

 

1)የጓሮ አትክልቶትን ከነ ቀንድአውጣ እና ሌሎች ቅጠል በስተው ከሚያበላሹ ትሎች ለመከላከል:-

የዕንቁላል ቅርፊቱን ሰበር ሰበር አድርገው የጓሮ አትክልት ያለበት አፈርና ቅጠሎች ላይ በተን በተን ጣል ጣል አድርጉበት። እንደ ቀንድ አውጣ የመሳሰሉት ለስላሳ ሰውነት ያላቸው ትሎች ስለሚቆርጣቸው ይሸሹታል።

 

2) የጓሮ አትክልት አፈርን ልማትነቱን ለመጨመር:-

የእንቁላል ቅርፊቱን ደቀቅ አድርገው የጓሮ አትክልት አፈር ላይ በተን ማድረግ የእንቁላል ቅርፊት በካልሲየም እጅግ የበልፀገ ነገር ስለሆነ የአፈሩን ለምነት ይጨምራል። በዛም ምክንያት የእንቁላል ውርፊት ደቀቅ አድርጎ የአትክልት አፈር ላይ መበተን የትኛውንም አትክልት በተለይ ቲማቲምን እንደሚጠቅምና ቶሎ እንደሚያሳድግ በመረጃ የተረጋገጠ ነው።

 

3) ለዶሮዎች እንዲመገቡ መስጠት:-

ዶሮዎች በተለይ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎች ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ መጀመሪያ የእንቁላል ቅርፊቱን በደንብ በመቀቀልና በማድረቅ ከዛም በማድቀቅ የደቀቀውን ቅርፊት ከሌላ ምግብ ጋር በመደባለቅ ለዶሮዎች መስጠት ይቻላል። ይሄም ለዶሮዎቹ በጣም ጠቃሚ ነው።

እሄንን ዘዴ ለሌሎች የቤት እንስሳትም በመጠቀም አጥንታቸው ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ ይቻላል።

 

4) ለሰውነታችን ካልሲየምን ለመመገብ:-

ካልሲየም የሚባለው ንጥረ ነገር ለሰውነታችን በተለይ ለአጥንቶቻችንና ለጥርሶቻችን ጥንካሬና ጤንነት አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ነው።

የእንቁላል ቅርፊት ድግሞ በካልሲየም እጅግ በጣም የበለፀገ ነው።

ስለዚህ የእንቁላል ቅርፊትን መጀመሪያ ከባክቴሪያ ነፃ ለማድረግ ከአምስት ደቂቃ በላይ በሚንተከተክ ውሃ ውስጥ ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በሚንተከተከው ውሃ ውስጥ እንደገባ አረጋግጦ መቀቀል። ከዛ ከተቻለ በኦቭን አሊያም እንዲሁም በደንብ አድርቆ በደንብ መውቀጥ። የተወቀጠውን በሆነ ዕቃ አድርጎ ማስቀመጥ። እሱን እንደገንፎ፣ ወጥ ወይም አጥሚት አይነት ነገሮች ውስጥ በተን እያደረጉ መጠቀም ለሰውነታችን በተለይም ለአጥንቶቻችንና ለጥርሶቻችን ጥንካሬና ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።

ምንጭ፡-tekamii.blogspot.

 

  

Related Topics