የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን/መቀነስ የሚገባበት ምክንያቶች
የሚመገቡትን የጨዉ መጠን መመጠን/መቀነስ የሚገባበት ምክንያቶች
ጨዉ ለረጅም ጊዜ የሚታወቀዉ በደም ግፊት ጤንነት ላይ የረጅም ጊዜ ጠላትነት እንደላለቸዉና ችግር እንደሚፈጥር ነዉ ፡፡ ምንም እንኳ ሶዲየም ለሰዉነታችን ከሚያስፈልጉ አስፈላጊ ንጥረነገሮች ዉስጥ ቢመደብም ከመጠን በላይ ይህን ንጥረነገር መዉሰድ የደም ግፊትን እንደሚጨምር በጥናቶች ተረጋግጧል፡፡ ከመጠን ያለፈ ጨዉ (ሶዲያም) መመገብ የደም ግፊቱን እንኳ ባይጨምር በልብ፣ በደም ቧንቧ፣ በኩላሊትና በአእምሮ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡
ጨዉ በልብ፣ በደም ስሮች፣ በአእምሮና ኩላሊትዎ ላይ የሚኖረዉን ጫና/ጉዳት ለመቀነስ/ ለመከላከል
የቤት ምግብ መመገብ፡-
በቤትዎ የተሰራን ምግብ ሲመገቡ ምን ያህል ጨዉ ምግብዎ ላይ እንደሚጨምሩ መቆጣጠር ስለሚችሉ የቤት ምግብ ለመመገብ ይሞክሩ፡
አትክልት፣ ፍራፍሬና ሌሎች የምግብ ይዘታቸዉ ጥሩ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር
የተመጣጠነ የምግብ ይዘት ስለሚኖራቸዉና በዉስጣቸዉ እንደፖታሲየም ያሉ ንጥረነገሮችን ስለሚኖራቸዉ ለደም ቧንቧ ጤንነት መልካም ነገሮች ናቸዉ፡፡
ምንጭ፡- ሜዲካል መጽሄት ግንቦት-2008
Related Topics