በዕዉቀቱ በጎጃም ማንኩሳ በምትባል ገጠር ቢጤ ከተማ ተወለደ፡፡

በዕዉቀቱ ስዩም

 

Image result for በዕዉቀቱ ስዩም

 

በዕዉቀቱ በጎጃም ማንኩሳ በምትባል ገጠር ቢጤ ከተማ ተወለደ፡፡ ደብረማርቆስ ተማረ፡፡ የትዉልድ ዘመኑ 1972 ሀምሌ 12 ነዉ ከፍቅር እስከ መቃብር በዛብህ ቦጋለ ቀጥሎ በቅኔ መንፈስ የታወቀ ማንኩሴ ቢኖር እኔ ነኝ የሚለዉ በዕዉቀቱ በ1995 ዓ.ም ኗሪ አልባ ጎጂዎች የሚል ጎጆዎች የሚል የግጥም ስብሰባና በ1996 በረራ ቅጠሎች” የሚል የ ሽርፍራፊ ታሪኮች መድብል አሳትሟል፡፡ በፓፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ክንፋም ህልሞች የተሰኘዉን አጭር ልቦለድ አቅርቧል፡፡ ሌሎች ያለታተሙ የስነ ጹሁፍ  ስራዎችና የነገር ሀሳብ ጥናቶችም አሉት፡፡

በእዉቀቱ በ1993 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪዉን አገኘ ሲሆን አሁን በጹሁፍ ስራ ይተዳደራል፡፡

እንባዬን የት ላርገው
(በእውቀቱ ሥዩም)
ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው
ወዴት ልሸሽገው?

ምንጭ፡- ወንዞች እስኪሞሉ

 

  

Related Topics