የየቀኑን እራታቸውን የሚያበስሉት ቢልየነሩ ቢል ጌትስ

 

በየቀኑን እራታቸውን የሚያበስሉት ቢልየነሩ ቢል ጌትስ

 

Image result for ቢል ጌትስ

 

በዓለም ሃብታም ከሆኑ ሰዎች በቀዳሚነትየሚታወቁት የማይክሮሶፍት መስራቹ ቢልጌትስ፣ ምግባቸውን አብስለው ይመገባሉ ቢባልቀልድ ይመስላል:: ሆኖም ሲኤንቢሲ የማብሰልንጥቅም አስመልክቶ ይዞት በወጣው ዘገባ፣ ቢልጌትስ ምግባቸውን ማብሰል ከመውደዳቸውምበተጨማሪ፣ ሁልጊዜ በሚባል መልኩ ማታላይ ቤተሰቦቻቸው ለመመገብ የተጠቀሙባቸውንሰሃንና መጠጫዎች ያጥባሉ:: አንድ ወቅትላይ “ሰዎች ከእርሶ የማይጠብቁት ግንየሚያስደስትዎት ሥራ ምንድነው?” ተብለውየጠየቁት ቢልጌትስ፣”በየቀኑ ምሽት ምግብአበስላለሁ:: ሌሎች ሰዎች ይህንን በበጎ ፈቃድሲሠሩት ይችላሉ፣ እኔ ግን ስለምወደው ነው”ብለው ነበር::በቅርቡ የወጡ ጥናቶች፣ ምግብን ማብሰልምሆነ የተመገቡበትን ዕቃ ማጠብ ጭንቀትእንደሚቀንስና ፈጠራን እንደሚያጎለብትአስፍረዋል::ፍሎሪዳ ስቴት ዩኒቨርስቲ፣ የመመገቢያዕቃዎችን እንዲያጥቡ ያደረጋቸው ተማሪዎችየነበረባቸው ጭንቀት መቀነሱንና ለመስራትያላቸው ፍላጎት መነሳሳቱን አስታውቋል:: ዕቃበሚታጠብበት ውኃ ውስጥ ትኩረት ማድረግናየማጠቢያ ሳሙናዎችን ማሽተት አዕምሮእንደሚያነቃቃም ገልጸዋል::ዮኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በበኩሉ፣ ብዙየማያጨናንቁ ሥራዎችን መስራት አእምሮአዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥርና ችግር ፈቺሐሳቦችን እንዲያፈልቅ ያስችላል ብሏል::

ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ