የቲማቲም ድልህ ወይም ካቻኘ በእለት ተእለት ምግባችን ማባያ የምንጠቀምበ

 አስገራሚ የቲማቲም ድልህ (ካችአኘ(ketchup)) ጥቅሞች

 

 

Image result for ketchup

 

የቲማቲም ድልህ ወይም ካቻኘ በእለት ተእለት ምግባችን ማባያ የምንጠቀምበት የቲማቲም ውጤት ነው።በአብዘሀኛው ለሀም በርገር፣ሆትዶግ እንዲሁም ለድንች ጥብስ(ቺብስ) በሰፊው እንጠቀምበታለን ።

ካቻኘ በአብዛሀኛው ሰወች ለምግብ ማጣፈጫነት ተደርጎ ቢታሰብም ከፍተኛ የሆነ የላይኮኜን(lycopene) የተባለ ንጥረ ነገር ክምችት የያዘ ሲሆን ይህ ንጥረ ነገር ሲሆን በተጨማሪም የድኝ (sodium) ክምችት ይዟል።

1:- ለልብ ጤንነት

ላይኮኜን(lycopen) በሰውነታችን ውስጥ የሚካሄደውን የአንቲ -ኦክሲዳንት (Antioxidant) ስራን በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲካሄድ ይረዳል።

ይህ የአንቲ -ኦክሲዳንት (Antioxidant) ስራ በሰውነታችን ውስጥ ባሉ የደም ቧንቧ ግርግዳዎች ላይ የሚለጠፋ የስብ ክምችትን ይቀንሳል። የስብ ክምችት በጨመረ ቁጥር የደም ቧንቧችን በመጥበብ ከፍተኛ ለሆነ የልብ ችግር ያጋልጠናል።

2:- የጡት ካንሰርን ይከላከላል፦

በመረጃ የተደገፉ ጥናቶች እንደሚያሳዬት ካቻኘ በከፍተኛ ደረጃ የጡት ካንሰርን ይከላከላል።በካቻኘ ውስጥ የሚገኘው ይህ ላይኮኚን የተባለ ንጥረ ነገር የአንቲ -ኦክሲዳንት (Antioxidant) እና የሰውነት መጉረብረብ (Anti-imflammatory) የመከላከል አቅም አለው ይህ ደግሞ የጡት ካንሰር ይከላከላል።

3:- ለአጥንት ጤንነት፦

በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ጥናቶች እንዳሳዪት በተለይ በሴቶች ከ40-45 እድሜ አካባቢ የወር አበባ ማየት በሚያቆሙበት ጊዜ በአጥንት ህዋስ ላይ የሚያጋጥም የሆነ የኦክሲዴሽን(oxidation) ስራ ይካሄዳል።

ይህ oxidation Process የአጥንት መሳሳትን ና ህመም ያስከትላል። ካቻኘ መመገብ ከዚህ ችግር እራሳችንን ለመከላከል ይረዳናል።

4:- ለቆዳ ውበት፦

በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ የቲማቲም ካቻኘ ስንመገብ በሰውነታችን ቆዳ ውስጥ የሚገኝ ከፀሀይ ጨረር የሚከላከሉልን እንደ carotenoids የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮች ክምችት እንዲጨምር ያደርጋል ይህ ደሞ ያማረና የለሰለሰ ቆዳ እንዲኖርን ይረዳናል።

5:- የወንድ የዘር ፍሬ መጠን ይጨምራል

ካቻኘ በሚመገብ ወንዶች ላይ በተደረገ ጥናት ከማይመገብ ወንዶች በ70% የዘር ፍሬ መጠን ጨምሮ ተገኝቶአል እንዲሁም በመሀፀን ውስጥ የዘር ፍሬ የሚጎዝበትን ፍጥነት እንዳደረገው ጥናቶች አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡-  ኢትዮጤና

 

 

  

Related Topics