የቀይ ስር፣ ካሮት እና አፕል ጭማቂ ለካንሰር እና ኩላሊት ህመም

የቀይ ስር፣ ካሮት እና አፕል ጭማቂ ለካንሰር እና ኩላሊት ህመም

 

የቀይ ስር፣ ካሮት እና አፕል ጭማቂ ለካንሰር እና ኩላሊት ህመም

 

ጊዜ አደገኛ እና ገዳይ የሚባሉ በሽታዎችን በቀላሉ እና ቤት ውስጥ በሚያዘጋጇቸው ውህዶች መከላከልና መቆጣጠር እንደሚቻል ይነገራል።

እንደ ካንሰር፣ ኩላሊት፣ የደም ግፊትና መሰል በሽታዎች ደግሞ በዚህ መልኩ ይጠቀሳሉ።

ቀይ ስር፣ ካሮት እና አፕልን አንድ ላይ በማዋሃድ ደግሞ እነዚህንና ሌሎችንም በሽታዎች መከላከል እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ሶስቱን የአትክልትና የስራ ስር ዘሮች በጭማቂ መልክ በማዘጋጀት መጠቀም፥ ካንሰርን፣ ኩላሊትና ተያያዥ ህመሞችን፣ የደም ቧንቧ መዘጋትን፣ አልሰር የሚባለውን ከባድ ቁስለትን መከላከል ያስችላል።

ከዚህ ባለፈም የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን በማሳደግ ከአላስፈላጊ የጤና ስጋት ነጻ እንዲሆኑም ያደርጋል።

ለዚህ የሚያስፈልገው ደግሞ አንድ ቀይ ስር፣ ሁለት ካሮት እና አንድ አፕልን ማዘጋጀት ነው።

 

አዘገጃጀት፦

በቅድሚያ ቀይ ስሩን በደንብ አጥቦ መጭመቅ እና ጭማቂውን ብቻውን ለአንድ ሰአት ያክል ማቀዝቀዣ ውስጥ ማቆየት።

ከአንድ ሰአት በኋላ ደግሞ በደንብ ታጥበው ከተዘጋጁት የካሮት እና አፕል ጭማቂዎች ጋር ማዋሃድ።

ከዚያም ዘወትር ማለዳ ቁርስ ከመመገብዎ ከግማሽ ሰአት በፊት ይህን ውህድ መጠጣት።

የቀይ ስር ጭማቂው ብቻውን አንድ ሰአት ማቀዝቀዣ ውስጥ ማቆየት እንዳለብዎት ግን እንዳይረሱ ከዛ በፊት ከሁለቱ አትክልቶች ጋር ማዋሃድ ጉዳት ስለሚያስከትል።

 ምንጭ፥ choosehealthylife.

 

 

  

Related Topics