ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ለህመም ማስታገሻነት

ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ለህመም ማስታገሻነት

 

ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ለህመም ማስታገሻነት

 

በእነዚህ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የሚያጋጥሙንን የህመም ስሜቶች በደቂቃዎች ውስጥ ማስታገስ እንችላለንም ብለዋል።

ጀርባችን፣ ትከሻችን፣ አንገታችን፣ ጉልበታችን እንዲሁም የእጅ መገጣጠሚያ አካላችን ላይ ድንገተኛ የህመም ስሜት በሚሰማን ጊዜም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አካላዊ

 

እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይመከራል።

1.    የጀርባ ህመም

ጀርባችን ታችኛው ወይም ላይኛው ክፍል ላይ ድንገት የህምም ስሜት በሚሰማን ጊዜ እዛው በተቀመጥንበት ቦታ ሆነን ቀለል ባለ አካላዊ እንቅስቃሴ ማስታገስ እንችላለን።

 

የላይኛው የጀርባ ክፍል  የህመም ስሜት በሚሰማን ጊዜ

- ራሳችንን ማቀፍ

- ይህንን ለማድረግም የቀኝ እጃችንን በግራ ትከሻችን ላይ እንዲሁም የግራ እጃችንን ደግሞ በቀኝ ትከሻችን ላይ ማስቀመጥ

- በመቀጠልም ቀስ እያልን አየር ወደ ውስጥ በመሳብ መልቀቅ

- ለግማሽ ደቂቃ ያህል በደንብ ይዘን መቆየት

- ከዚያም ቀስ እያልን መልቀቅ

በታችኛው የጀርባችን ክፍል ድንገት የህመም ስሜት ሲሰማን ማድረግ ያለብን እንቅስቃሴ፦

 

-  ወንበር ላይ ቀጥ ብለን መቀመጥ

-  ጉልበታችንን ወደ ደረታችን በማስጠጋት ከፍ አድርገን መያዝ

-  ለግማሽ ደቂቃ ያህል ባለበት ይዘን መቆየት

-  ከዚያም በቀስታ እግራችንን ወደ ታች ማውረድ

-  ይህንን እንቅስቃሴ በሌላኛው እግራችንም ደግመን መተግበር።

 

2.  የትከሻ ህመም

ትከሻችን አካባቢ የህመም ስሜት በሚሰማን ጊዜ ቀለል ባለ እንቅስቃሴ ለማስታገስ፦

- ትከሻችንን ወደ ጆሯችን ከፍ ማድረግ እና በደንብ ወደ ውስጥ አየር ማስገባ

- ትከሻችንን ከፍ ባደረግንበት ለ3 ሰከንዶች ያህል ማቆየት

- ቀስ እያልን ወደ ውጪ እየተነፈስን ትከሻችንን መልቀቅ

- ይህንንም ለ10 ደቂቃ ያህል ሳናቋርጥ ደጋግመን መተግበር።

 

3.    የአንገት ህመም

- በመጀመርያ ወንበር ላይ ቀጥ ብለን ተስተካክለን መቀመጥ

-  በመቀጠልም አንገታችንን ወደ አንደኛው ጎን ትከሻችንን ማዘንበል

-  ለግማሽ ደቂቃ ያህል ባለበት ወይም ባዘነበልንበት መቆየት

-  ይህንኑ እንስቃሴ ባልሰራንበት በኩል ለ10 ጊዜ ያህል ደጋግመን መስራት አለብን።

 

4.  የእጅ መገጣጠሚያ ህመም

-  ሁለቱንም እጃችንን በቦክስ መልክ መጨበጥ

-  በመቀጠልም ሁለቱንም እጆቻችንን ወደ ፊት በማምጣት መገጣጠሚያ ስፍራ እጃችንን ወደ ላይ እና ወደ ታች እንዲሁም ወደ ጎን በማድረግ በሁሉም አቅጣጫ ማሽከርከር

-  ይህንንም በሁሉም አቅጣጫ ለ10 ጊዜ ያህል ደጋግመን ማንቀሳቀስ።

 

5. የጉልበት ህመም

-  በመጀመሪያ ወንበር ላይ ቀጥ ብለን ተስተካክለን መቀመጥ

-   ቀስ እያልን በአንድ ጊዜ ከመቀመጫችን ላይ በመነሳት መቆም

-  ተመልሰን ቀስ እያልን መቀመጥ

-  ለ10 ጊዜ ያህል ደጋግመን መስራት ይኖርብናል።

 

 

ምንጭ፦ www.webmd.com

 

  

Related Topics