ፊትን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታይ ጠባሳ እና ምልክት ለ

ለቆዳ እና የፊት ላይ ጠባሳዎች

 

ለቆዳ እና የፊት ላይ ጠባሳዎች

 

ፊትን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታይ ጠባሳ እና ምልክት ለብዙ ሰዎች አስቸጋሪ እና አሳሳቢው የውበት ጉዳይ ነው።

ይህን መሰሉ ችግር፦ በተባይ ንክሻ፣ በእሳት እና የፈላ ውሃ አደጋ፣ ቆዳ ላይ በሚወጣ ሽፍታ፣ የቀዶ ጥገና ጠባሳዎች፣ በክትባት አማካኝነት ይከሰታል።

ይሁን እንጅ ይህን ችግር ከህክምና በተጨማሪ በቤት ውስጥ በቀላሉ በሚዘጋጁ ውህዶች ማከም እና ማስወገድ ይቻላል።

ለዚህም ቁልቋል፣ የወይራ ዘይት፣ ሎሚ፣ ማር እንዲሁም የአፕልና ቱፋ ጭማቂን መጠቀም ይቻላል።

አዘገጃጀት፦ የቁልቋሉን ጫፍ በመቅጠፍ ካጸዱ በኋላ በጥንቃቄ በመላጥ ፈሳሹን ሽፍታው ወይም ጠባሳው ያለበት ቦታ ላይ መቀባት እና ለግማሽ ሰአት ማቆየት።

ከተቀቡት በኋላ በንጹህ እጅ ፈሳሹ ሁሉም ቦታ ላይ እንዲደርስ አድርጎ ማሸት እና ከተባለው ጊዜ በኋላ መታጠብ። ይህን ከተቻለ በቀን ሁለት ጊዜ ማድረግ።

የተጎዳውን የሰውነት ክፍል በንጹህ ውሃ በመታጠብ የወይራ ዘይት መቀባት እና ሁለት ወይም ሶስት ጣትዎን በመጠቀም እያከበቡ በማሸት ማዳረስ።

ይህንን ለ30 ደቂቃ ያክል ቦታው ላይ ማቆየት እና ከተባለው ጊዜ በኋላ በንጹህ ፎጣ መጥረግ፤ መታጠብ አይመከርም።

ይህንን አስፈላጊውን ለውጥ እስኪያገኙ ድረስ በየቀኑ መደጋገም፤ በቪታሚን ኢ የበለጸገው ይህ ዘይት የቆዳን ወዝ እና ልስላሴ ለመመለስ ይረዳል።

ማታ አልጋዎ ከመግባትዎ በፊት ሰውነትዎን በማጽዳት ወለላ ማሩን የተጎዳው ክፍል ላይ መቀባትና ሁለት ጣትዎን በመጠቀም በክቡ ማሸት እና ማዳረስ።

ይህን ካደረጉ በኋላ መተኛት እና ማለዳ ሲነቁ ጥቂት ለብ ባለ ውሃ መታጠብ ይህንንም ለውጥ እስኪመለከቱ ድረስ መደጋገም።

ማር በውስጡ በያዘው ውህድ ሳቢያ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን በማስወገድ ለአዲስ እና ንጹህ የቆዳ ጤንነት ማደግ ይረዳል።

የአፕል ወይም የቱፋ ጭማቂን በጥጥ ነገር በመምጠጥ የተጎዳው ክፍል በአግባቡ መቀባት እና ለ10 ደቂቃ ያክል መቆየት።

ከዚያም በንጹህ ውሃ ለቅለቅ ማድረግ፤ ይህንንም ለሁለት ሳምንት በየቀኑ መደጋገም።

የሎሚ ጭማቂን ወይም ሎሚውን ሰንጥቆ የተጎዳውን ቦታ መቀባት፤ ቦታው ላይ ለ10 ደቂቃ ማቆየት ከዚያም ለብ ባለ ውሃ መለቃለቅ።

ይህንን ለውጥ እስኪመለከቱ ድረስ መደጋገም፤ ሁሉንም አይነት ውህዶች ተቀብተው ካስወገዱ በኋላ የቆዳ ማለስለሻ ሎሺን መቀባቱ ይመከራል።

 

ምንጭ፦ stethnews.com