ሰዎች ፊት ቆመን ንግግር የማድረግ ፍራቻን ለማስወገድ እንዲህ ብናደርግስ

ሰዎች ፊት ቆመን ንግግር የማድረግ ፍራቻን ለማስወገድ እንዲህ ብናደርግስ…?

 

ሰዎች ፊት ቆመን ንግግር የማድረግ ፍራቻን ለማስወገድ እንዲህ ብናደርግስ…?

 

አብዛኞቻችን በተለያዩ አጋጣሚዎች በርከት ያሉ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ንግግር ለማድረግ እንገደድ ይሆናል።

ታዲያ በዚህ ጊዜ በርካቶቻችን ላይ የፍራቻ ምልክቶች ሲታዩ ይስተዋላል፤ ከዚህም የተነሳ በርካቶች መናገር የፈለጉትን እንኳ በቅጡ ሳያስተላልፉ ሲቀሩ ይስተዋላል።

ይህ ግን ተገቢ አይደለም ይላሉ በአሜሪካ ዋሽንግተን በሰዎች ፊት ቆሞ ንግግር እንዴት ማድረግ ይቻላል በሚል ዙሪያ ስልጠና የሚሰጡት አሊሰን ሻፒራ።

እንደ አሊሰን ሻፒራ ገለጻ፥ ንግግር ለሚያደርግ ሰው የመጣበት ስፍራ፣ የኑሮው ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ወይም የመጣበት የስራ የሃላፊነት እንደ መስፈርትነት መቅረብ

የለበትም፤ ማንኛውም ሰው ንግግር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ስፍራ ማድረግ ይችላል ይላሉ።

አሊሰን ሻፒራ፥ ነገር ግን ንግግር ከማድረጋችን በፊት መጀመሪያ እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን ብንጠይቅ የተሻለ ለመዘጋጀት ይረዳናል ይላሉ።

 

ጥያቄዎቹም፦ ተዳሚዎቼ ወይም አድማጮቼ እነ ማን ናቸው?

                    ንግግሩን የማደርግበት አላማ ምንድነው?

                    ይህን ንግግር እንዳደርግ ለምን ተመረጥኩ?

 

እነዚህን ጥያቄዎች ንግግር ከማድረጋችን በፊት ራሳችንን በመጠየቅ መልስ ከሰጠንበት የተሻለ ለመዘጋጀት እና የፈለግነውን መልእክት በአግባቡ ያለ ፍራቻ ለማስተላላፍ ይጠቅመናል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰዎች ፊት ቆመን ንግግር በምናደርግበት ወቅት የሚያጋጥመንን ጭንቀት እና መረበሽ ለማስቀረት ይረዳናል ያሉትን ነጥቦችም ዘርዝረዋል።

 

እነዚህም፦

1. ራሳችንን ፈታ ማድረግ፦ ንግግር ከማድረገታችን በፊት እና በምናደርግበት ጊዜ ራሳችነን ፈታ በማድረግ በነጻነት ስሜት ማቅረብ።

2. እይታን መጠቀም፦ ንግግር በምናደርግበት ጊዜ ከታዳሚዎቻችን ጋር ቀጥታ የአይን ግንኙነት እንዲኖረን ማድረግም ፍራቻን ለማውሰገድ ይረዳል ተብሏል።

3. ቀደም ብሎ መለማመድ፦ ንግግር ከማድረጋችን በፊት ንግግር የምናደርግበትን ነገር ለብቻችን ሆነን ደጋግመን መለማመ,ድ በሰዎች ፊት ስንቀርብ የበለጠ በራስ መተማመን እንዲሰማን ያደርጋል።

4. እሳሳታለሁ የሚል ፍራቻን ማስወገድ፦ ሰዎች ንግግር ማድረግ እንዲፈሩ ከሚያደርጋቸው መክንያቶች ውስጥ አንዱ ስህተተን መፍራት ነው።

በንግግር ጊዜ ስህተት በማንኛውም ጊዜ ሊፈጠር የሚችል መሆኑን ራስን በማሳመን መጀመር እና ቢፈጠር እንኳ እንዴት ማስተካከል አለብኝ የሚለውን ማሰብ መልካም ነው።

 

ምንጭ፦ www.share.america.gov

 

  

Related Topics