አልኮልን ከመጠን በላይ መውሰድ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች ላይ ምን ጉ

አልኮልን ከመጠን በላይ መውሰድ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች ላይ ምን ጉዳት ያስከትል ይሆን?

 

አልኮልን ከመጠን በላይ መውሰድ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች ላይ ምን ጉዳት ያስከትል ይሆን?

 

የአልኮል መጠጥን ከልክ በላይ መውሰድ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ስለሚሆን አልኮልን መጥኖ መጠቀሙ ይበጃል ይላል የሜንስ ሄልዝ ዘገባ።

የአልኮል መጠጥን መጥኖ መውሰዱ በተቃራኒው ለሰውነታችን የተለያዩ ጥቅሞችን ያስገኝልናል።

ቢራም ይሁን  ወይን አልያም ውስኪ አንዴ በተጎነጨን ቁጥር በሰውነታችን ውስጥ ለሁለት ሰዓታት በሚኖረው ቆይታ በደማችን በኩል አድርጎ የማይነካው የሰውነታችን ክፍል እንደሌለ ነው ዘገባው የሚናገረው።

የምንወስደው  የአልኮል መጠንም በጉበታችን ላይ ሊደርስ የሚችለውን የአደጋ መጠንም በዚያው ልክ ይወስነዋል።

ብዙዎቻችን የአለኮል መጠጥ መጎንጨት እንደምንወድ የታወቀ ነው፣ ይሁንና በቀን የምንወስደውን የአልኮል መወሰን ግን እጅግ አስፈላጊ ነው።

በቀን ከሁለት ብርጭቆ ያልበለጠ  አልኮል መውሰድ በሰውነታችን የስኳር መጠንን ዝቅ የማድረግ እና የፈ-ራ ችሎታ አቅማችንን የሚያሳዴግ እንደሆነም ነው ጥናቶች የሚያመለክቱት።

አልኮል ተመጥኖ ከተወሰደ በተለምዶ ቦርጭ ያስከትልብናል ከሚለው አስተሳሰብ በተቃራኒው በወገብ ዙሪያ የሚታይ አላስፈላጊ ቦርጭን ያስወግዳል።

 

ነገርግን አልኮልን ከልክ በላይ ከወሰድን በሚከተሉት የሰውነት ክፍሎቻችን ላይ ጉዳትን ያስከትላል።

 

1.አንጎል 

ነገሮችን ከመዘንጋት ጀምሮ መረጃዎች እንዲዛቡ እና በትክክል እንዳናገናዝብ ያደርጋል።

2.ቆዳ

የሰውነታችን ቆዳ እና የአይናችን ነጩ ክፍል እንዲቀላ ያደርጋል ።

3.ጡንቻ

ጡንቻዎቻችን እንዲዝሉ በማድረግ ስራ ለመስራትም ሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲሳነን ያደርጋል

4.ልብ

በቀን ከሁለት ብርጭቆ ያልበለጠ  አልኮል መጎንጨት የልብ ምትን ሲያስተካክል በአንፃሩ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠን ለልብ ህመም ሊዳርገን ይችላል።

5.ጨጓራ

ከመጠን በላይ የሆነ የአልኮል አወሳሰድ ከማቃጠል ስሜት አልፎ ጨጓራን እስከማቁሰል ይደርሳል።

6.የወንድ የዘር ፍሬ

የወንድ የዘር ፍሬ የዘር ፍሬ የመዋኘት አቅምን በእጅጉ ከመቀነስ ጀምሮ  የዘር ፍሬው ጥራትን እስከመቀነስ የደረሰ ችግርን ያስከትላል።

ታዲያ የምንወስደውን  የአልኮል መጠጥ መጠን መመጠኑ አይበጅም ትላላችሁ?

 

ምንጭ፦ Men's Health

 

  

Related Topics