የኢንፍሉዌንዛ ክትባት እርስዎ ማወቅ የሚያስፈልግዎ

የኢንፍሉዌንዛ ክትባት እርስዎ ማወቅ የሚያስፈልግዎ

 

Image result for የኢንፍሉዌንዛ ክትባት

 

1 መከተብ ለምን ያስፈልጋል?

ኢንፍሉዌንዛ (“ጉንፋን”) በአሜሪካ አካባቢዎች በየክረምቱ፣ በተለይም በጥቅምት እና ግንቦት መካከል የሚስፋፋ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ጉንፋን የሚመጣው በኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ሲሆን በሳል፣ በማስነጠስ፣ እና በንክኪ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ማንኛውም ሰው ጉንፋን ሊይዘው ይችላል፣ ነገር ግን ጉንፋን የመያዝ አደጋ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ነው፡፡ ምልክቶቹ በድንገት ሊመጡ እና ለበርካታ ቀናት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

• ትኩሳት/ብርድ ብርድ ማለት

• የጉሮሮ መቁሰል

• የጡንቻ ህመም

• ድካም

• ሳል

• ራስ ምታት

• ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ

ጉንፋን አንዳንድ ሰዎችን ከሌሎች በበለጠ ሊያሳምማቸው ይችላል፡፡ እነዚህም ህጻናት፣ 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ትልልቅ ሰዎች፣ እርጉዝ ሴቶች፣ እና የተወሰኑ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች -ለምሳሌ ልብ፣ ሳንባ ወይም የኩላሊት በሽታ ወይም የተገደለ የበሽታ መከላከል አቅም ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የጉንፋን ክትባት በተለይ ለእነዚህ ሰዎች እና ከእነሱ ጋር ንክኪ ላለው ሰው ጠቃሚ ነው፡: ጉንፋን ወደ ኒሞኒያ ሊቀየር ይችላል እናም ያሉትን የጤና ሁኔታዎች አደገኛ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በሕጻናት ላይ ተቅማጥ እና አካላዊ መዳከም ሊያመያ ይችላል፡፡ በእያንዳንዱ አመት አሜሪካ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጉንፋን ይሞታሉ፣ እንዲሁም በርካቶች ሆስፒታል ይገባሉ፡፡ የጉንፋን ክትባት ጉንፋንን እና የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመከላከል ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ በተጨመሪም የጉንፋን ክትባት ጉንፋን ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ይከላከላል፡፡

2 የተገደለ የጉንፋን ክትባት

ሁለት ዓይነት የጉንፋን ክትባቶች አሉ፡

የተዳከመ የጉንፋን ክትባት ሊሰጥዎ ይችላል፤

 

ይህም ማንኛውም አይነት በሕይወት ያለ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በውስጡ የያዘ አይደለም፡፡ በመርፌ መወጋት ይሰጣል፣ እና በተለምዶ “ፍሉ ሻት” በመባል ይጠራል፡:

 

የጉንፋን ክትባት በየአመቱ እንዲወሰድ ይመከራል፡፡ ከ6 እስከ 8 ወር ያሉ ሕጻናት በተከተቡበት የመጀመሪያ አመት ሁለት መጠን መውሰድ አለባቸው፡፡ የጉንፋን ቫይረስ ሁልጊዜ ተለዋዋጭ ነው፡፡የእያንዳንዱ አመት የጉንፋን ክትባት በዚያ አመት በሽታ ሊያመጣ የሚችለውን የጉንፋን ቫይረስ ለመከላከል ይሰጣል፡፡ ምንም እንኳን የጉንፋን ክትባት ሁሉንም የጉንፋን አይነቶች ባይከላከልም፤ በሽታውን ለመከላከል ያለን ተቀዳሚ አማራጭ ነው፡፡ የተገደለ የጉንፋን ክትባት 3 ወይም 4 የተለያዩ የጉንፋን አይነቶችን ይከላከላል፡፡ Iከክትባት በኋላ የመከላከል አቅም እስኪጎለብት ድረስ 2 ሳምንት ይወስዳል፣ እንዲሁም የመከላከል አቅሙ ከበርካታ ወራት እስከ አመት ድረስ ይዘልቃል፡፡አንዳንድ በኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ የማይከሰቱ ሕመሞች በአብዛኛው ጉንፋን እንደሆኑ ተደርገው በስህተት ይወሰዳሉ፡፡ የጉንፋን ክትባት እነዚህን ሕመሞች አይከላከልም፡፡ ኢንፍሉዌንዛን ብቻ ነው የሚከላከለው፡፡ 65 ዓምት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዛውንቶች የ “ከፍተኛ-መጠን” የጉንፋን ክትባት አለ፡፡ ክትባቱን የሚሰጥዎ ሰው ተጨማሪ ነገሮችን ሊነግርዎ ይችላል፡፡Sአንዳንድ የተገደለ የጉንፋን ክትባቶች በጣም ጥቂት መጠን ያለው ሜሪኩሪ መሰረት ያለው ቲሜሮሳል የተባለ ማቆያ ይይዛሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በክትባት ውስጥ የሚገኝ ቲሜሮሳል ጉዳት የለውም፣ ነገር ግን ማቆያ የሌላቸው የጉንፋን ክትባቶችም አሉ፡፡

 

3 አንዳንድ ሰዎች የጉንፋን ክትባት መውሰድ የለባቸውም

ክትባቱን ለሚሰጥዎ ሰው የሚከተለውን ይንገሩት፡

• አደገኛ (ለህይወት የሚያሰጋ) አለርጂ ካለብዎ፣ ይሕም የእንቁላል አለርጂን ይጨምራል፡፡ የጉንፋን ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለህይወት የሚሰጋ አለርጂ ገጥሞዎት የሚያውቅ ከሆነ፣ ወይም ለማንኛውም የዚህ ክትባት ክፍል አለርጂ ካለብዎ ክትባቱን በየትኛውም መጠን እንዳይወስዱ ይመከራሉ፡፡

• ጉሊያን-ባሬ ሲንድረም ካለብዎ (ጂቢኤስ በመባል የሚታወቅ በአደገኛ ሁኔታ ፓራላይዝ የሚያደርግ የበሽታ አይነት)፡፡ የጂቢኤስ ታሪክ ያላቸው አንዳንድ ሰዎች ይሕንን ክትባት እንዲወስዱ አይመከሩም፡፡ ይህንን ከሐኪምዎ ጋር መወያየት አለብዎ፡፡

• ጤንነት ካልተሰማዎ፡፡ እስኪሻልዎት ድረስ እንዲቆዩ ሊመክሩዎ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተመልሰው መምጣት ይኖርብዎታል፡፡

 

ሌላኛው እና የተለየው፣ በሕይወት ያለ፣ የተዳከመ የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ሲሆን በአፍንጫ ውስጥ በመጨመር ይሰጣል፡፡ ይህ ክትባት በተለየ የክትባት መረጃ ቃላት ይገለጻል፡፡

 

4 የክትባቱ አስጊ ውጤቶች

እንደማንኛውም መድኃኒት፣ ክትባትም የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን ቀላል እና ቶሎ የሚድኑ ናቸው፡፡አደገኛ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን በጣም አልፎ አልፍ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ የተገደለ ኢንፍሉዌንዛ ክትባት በሕይወት ያለ ቫይረስ አይዝም፡፡ ስለዚህም ከዚህ ክትባት ጉንፋን መያዝ አያጋጥምም፡፡ ቀላል ራስን የመሳት ሁኔታዎች እና ተያያዥ ምልክቶች (ለምሳሌ የመንቀጥቀት እንቅስቃሴዎች) ክትባትን ጨምሮ ከማንኛውም የህክምና ስራ በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ከክትባት በኋላ ለ15 ደቂቃ መቀመጥ ወይም ጋደም ማለት ራስን ከመሳትም ሆነ በመውደቅ ከሚመጡ አደጋዎች

ይከላከላል፡፡ የመፍዘዝ ስሜት ከተሰማዎት፣ እይታዎ ላይ ለውጥ ከመጣ ወይም ጆሮዎ ላይ የሚደውል ድምጽ ከተሰማዎት ለሐኪምዎ ይንገሩ፡፡

ከተገደለ ጉንፋን ክትባት በኋላ የሚያጋጥሙ ቀላል ችግሮች፡

• ክትባቱ በተሰጠበት ቦታ ላይ መቁሰል፣ መቅላት፣ ወይም ማበጥ

• አይን መቆርቆር፣ ማበጥ፣ መቅላት ወይም ማሳከክ፤ ሳል

• ትኩሳት

• የህመም ስሜት

• ራስ ምታት

• ማሳከክ

• ድካም

እነዚህ ችግሮች የሚያጋጥሙ ከሆነ እንኳን፣ ክትባቱ እንደተሰጠ ወዲያው ይጀምሩ እና ለ1 ወይም ለ 2 ቀናት ይዘልቃሉ፡፡

• ከተገደለ ጉንፋን ክትባት በኋላ የሚያጋጥሙ መካከለኛ ችግሮች፡

የተገደለ ጉንፋን ክትባት እና ኒሞኮካል ክትባት (PCV13) በተመሳሳይ ጊዜ የወሰዱ ህጻናት በትኩሳት ምክንያት ለመዳከም ይጋለጣሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ሐኪምዎን ይጠይቁ፡፡ የጉንፋን ክትባት የሚወስድ ልጅ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞት የሚያውቅ ከሆነ ለሐኪምዎ ይንገሩ፡፡

ከተገደለ ጉንፋን ክትባት በኋላ የሚያጋጥሙ አደገኛ ችግሮች፡

• ከማንኛውም ክትባት በኋላ አደገኛ የአለርጂ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል (ከሚሊዮን መጠኖች ውስጥ 1 የሚከሰት)፡፡

• የተገደለ ጉንፋን ክትባት ከጉሊያን-ባሬ ሲንድረም (ጂቢኤስ) ጋር የሚገናኝበት አነስተኛ አጋጣሚ አለ፣ ክትባቱን ከወሰዱ ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ ከ1 ወይም 2 ያልበለጡ አጋጣሚዎች ናቸው ያሉት፡፡

ይህም በጉንፋን ምክንያት ከሚመጣ፣ እና በጉንፋን ክትባት ምክንያት መከላከል ከሚቻል አደገኛ ችግር የሚያንስ ነው፡፡ የክትባቶች ደህንነት ሁልጊዜም ቁጥጥር ይደረግበታል፡፡

 

5 አደገኛ የሆነ ውጤት ቢፈጠርስ?

ምን መመልከት አለብኝ?

• የሚያሳስብዎትን ማንኛውንም ነገር ይመልከቱ፣ ለምሳሌ የአደገኛ አለርጂ ምልክቶች፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ወይም የባህርይ ለውጥ፡፡ የአደገኛ አለርጂ ምልክቶች የቆዳ መቆጣት፣ የፊት እና ጉሮሮ ማበጥ፣

የመተንፈስ ችግር፣ ፈጣን የልብ ምት፣ መፍዘዝ እና ድካም፡፡ ይህም ከክትባቱ ከጥቂት ደቂቃዎች ወይም ሰዓታት በኋላ ይጀምራል፡፡

ምንጭ፡-ethioclinic.

 

  

Related Topics