ሙዝን ለመመገብ ትክክለኛው ጊዜ የቱ ነው ተብለው ቢጠየቁ “በደንብ ሲበስል

ሙዝን ለመመገብ ትክክለኛው ጊዜ

 

 ሙዝን ለመመገብ ትክክለኛው ጊዜ

 

ሙዝን ለመመገብ ትክክለኛው ጊዜ የቱ ነው ተብለው ቢጠየቁ “በደንብ ሲበስል” የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ ይታወቃል።

እርግጥ ነው በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ትክክል ነዎት።

ይሁን እንጂ ሙዝን በለጋነቱ መመገብ የሚገባቸው ሰዎች እንዳሉ እና የበሰለ አልያም ጥሬ ሙዝ መመገብ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድርባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በዚህ ፅሁፍም የበሰለ እና ጥሬ ሙዝ መመገብ አዎንታዊ እና አሉታዊ ገፅታዎቹን እንመለከታለን።

የበሰለ ሙዝ (ከ4 – 7)

በምስሉ ቁጥር 7 ላይ የምትመለከቱት አይነት በጣም የበሰለ ሙዝ በስነ ምግብ ባለሙያዎች ዘንድ በጣም ተመራጩ ነው።

ጥቁር ነጠብጣቦች (ጠቃጠቆ) ያለው ሙዝ ፀረ ካንሰር የሆኑ ይዘቶች እንዳሉትም ይናገራሉ።

በጣም የበሰለ ሙዝ ከፋይበር ጀምሮ የቫይታሚን ሲ፣ ፖታሲየም፣ ቫይታሚን ቢ እና ሌሎች አንቲኦክስደንቶች ይዘቱ ከፍተኛ መሆኑንም ነው የሚገልጹት።

የጃፓን ተመራማሪዎች ሙዝ ደንብ እስኪበስል (ቁጥር 7) መጠበቅ እነዚህን ጥቅሞቹን ለማሳደግ እንደሚረዳ ነው ያረጋገጡት።

ሌላው የበሰለ ሙዝ ጥቅም በሰውነታችን ውስጥ ለመዋሃድ ጊዜ የማይወስድ መሆኑ ነው።

ሙዝ በደንብ መብሰል ቢኖርበትም እስኪበላሽ ግን መጠበቅ አይኖርብንም። ሙዝን ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ ቶሎ እንዳይበላሽ እና ጠቃሚ ይዘቶቹን ለመጠበቅ ይረዳል።

በጣም መብሰላቸውን ካስተዋልን ግን ከሌሎች ፍራፍሬዎች ጋር ቀላቅለን በጭማቂ መልክ መጠቀም አልያም ለኬክ መስሪያ ማዋል ይቻላል።

በጣም የበሰለ ሙዝ በርካታ የጤና ጥቅሞች የሚያስገኝ ቢሆንም በጤና እክል ምክንያት ባይወስዱት የሚመከሩ ሰዎች አሉ።

የስኳር በሽተኞች የጣም በሰለ ሙዝ መብላት ከሌለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ የበሰለ ሙዝን ከለውዝ ቅቤ ጋር መመገብ ይችላሉ። በለውዝ ቅቤ ውስጥ የሚገኘው ስብ ከበሰለው ሙዝ የምናገኘውን ስኳር ለመሰባበር ይጠቅማል።

የበሰለ ሙዝ (4 – 7) ከጥሬው (1 – 3) ስምንት እጥፍ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያሳድግ መረጃዎች ያሳያሉ።

 

ያልበሰለ ሙዝ (1 – 3)

ያልበሰለ ወይም ጥሬ ሙዝም የራሱ የሆነ ጥቅም አለው።

ጥሬ ሙዝ ከበሰለው ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ስኳር እና ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ይዟል። በዚህም ለስኳር በሽተኞች (በተለይም ታይፕ 2) ተመራጭ ነው።

በሰውነታችን ውስጥ በፍጥነት የመዋሃድ ችግር እና ሆድን መንፋት ግን ትልቁ ያልበሰሉ ሙዞች አሉታዊ ጎን ነው።

በጣም ጥሬ ሙዝ (ቁጥር 1) ከፍተኛ የስታርች ይዘት ስላለውም በፍጥነት የመጥገብ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።

 

ምንጭ፦ http://supertastyrecipes.com/

 

  

Related Topics