የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው

 

የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው።

 

9ff0d41cd0c3a9f6a6115d6d2b000d58_L

 

ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል።

ሰውነታችን ኤክሶክራይን (exocrine) እና አፖክራይን (apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት።

ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን፥ የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው።

የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው።

ከመጠን ያለፈ ላብ እና የብብት ጠረንን ሁላችንም ልንከላከለው የምንፈልገው ጉዳይ ነው።

 

ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች ለሰውነት ጠረን መለወጥ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

ንፅህናን መጠበቅ፣ የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም፣ እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፣ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር፣ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣ ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን መጠቀም እና ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ ለችግሩ በመፍትሄነት ይነሳሉ።

 

የሰውነት ጠረንን በተለይም የብብት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ ነው።

 

ኬሚካሎችን ለመጠቀም ካልፈለጉና እየተጠቀሙት ያለው ዲዮድራንት የሚያረካ ውጤት ካላስገኘልዎ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቢሞክሯቸው መልካም ውጤት ያስገኛሉ ይላል የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ ገጽ ዘገባ።

 

1.  ቤኪንግ ሶዳ

ቤኪንግ ሶዳ የፍሪጅ እና ላውንደሪዎችን መጥፎ ጠረን ለማስወገድ እንደሚረዳው ሁሉ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚያግም ይነገራል።

ጥቂት ቤኪንግ ሶዳ ከበቆሎ ዱቄት ጋር በመቀላቀል ከብብት ውስጥ መክተት ቆዳችን ደረቅ እና ንጹህ እንዲሆን ያደርጋል።

 

2. የብብት ጸጉርን አለመላጨት

ሁሉም ነገር ሲፈጠር በምክንያት ነው፤ በሰውነታችን የሚወጡ ጸጉሮችም ለባክቴሪያ መፈጠር እና ለብብት ጠረን መቀየር ምክንያት የሚሆን እርጥበትን መሳብ አቅም አላቸው።

እናም የብብት ጸጉርን መላጨት (ሼቭ ማድረግ) ለባክቴሪያዎች መራባት እድል ይፈጥራል ማለት ነው።

የብብት ጸጉራችንን ከላጨን በኋላ የምንጠቀመው ቅባት ወይም ክሬምም የቆዳ መቆጣትን ሊያስከትል ስለሚችል የብብት ጸጉርዎን ከመላጨት ይቆጠቡ ይላል መረጃው።

 

3.  የሻይ ዛፍ ዘይት

የተለያዩ ቆዳ ነክ ችግሮችን እና መጥፎ የሰውነት ጠረንን ከሻይ ዛፍ በሚገኘው ዘይት ማከም ይቻላል።

የዚህ ዛፍ ዘይት በጸረ ባክቴሪያ እና ጸረ ፈንገስ ይዞታው ነው የሚታወቀው።

መጠነኛ የሻይ ዛፍ ዘይት ከሮዝ አበባ ውሃ ጋር ቀላቅሎ ብብትን መቀባት መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ይረዳል።

 

4. ተፈጥሯዊ ሳሙና

መላ ሰውነታችንን በተፈጥሯዊ ሳሙና መታጠብ መጥፎ የሰውነት ጠረንን ለማስወገድ ይጠቅማል።

ከወይራ ዘይት እና ሶዳ እንዲሁም ከፍየል ወተት የሚዘጋጁ ተፈጥሯዊ ሳሙናዎችን መጠቀም የቆዳ ውበትን ከመጠበቅ ባለፈ ማራኪ ጠረንን ያላብሳል ተብሏል።

 

5. አልኮል

እንደ ቮድካ ያሉ ሽታ አልባ የአልኮል መጠጦችን በስፕሬይ ብብትን መርጨት መጥፎ ጠረንን እና ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ ይረዳል።

ይሁን እንጂ አልኮል ልንጠቀም የሚገባው ልብስ ከመልበሳችን በፊት ነው።

 

6.    ሎሚ

ሎሚ የቆዳችንን ፒ.ኤች ደረጃ ለማስተካከል ያግዛል።

የሎሚ ቁራጭን ከብብታችን ስር በማድረግ ለ15 ደቂቃ መቆየት ቀኑን ሙሉ መልካም መዓዛ እንዲኖረን ይረዳል።

 

7.    የአፕል ጭማቂ

የአፕል ጭማቂ፣ ውሃ እና የሎሚ ጭማቂ በደንብ በማዋሃድ በመርጫ (ስፕሬይ) ውስጥ ማስገባት፤

ከዚያም ውህዱን በጠዋት ልብስ ከመልበሳችን በፊት ብብታችንን መርጨት ለመጥፎ ጠረን መከሰት ምክንያት የሆኑ ባክቴሪያዎችን ለማጥፋት ከፍተኛ ድርሻ አለው።

 

8.    ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ

ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድን ከውሃ ጋር በመቀላቀል ብብትን መርጨትም እንዲሁ የብብት ጠረንን ለማስተካከል እንደሚጠቅም ነው የሚነገረው።

በአጠቃላይ የሰውነት ጠረንን ለመጠበቅ በዋነኝነት ንጽህናችንን ለመጠበቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

 

 

ምንጭ፡- www.healthylifeland.com