ድንች ካለ እድሜ የሚከሰት ሽበትን ለመከላከል…

ድንች ካለ እድሜ የሚከሰት ሽበትን ለመከላከል…

 

ድንች ካለ እድሜ የሚከሰት ሽበትን ለመከላከል…

 

ጤናማው ሽበት የእድሜ መግፋትን አመላካች መሆኑ እሙን ነው።

ካለ እድሜ የሚከሰት ሽበት ግን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እጥረትን ተከትሎ የሚከሰት ነው።

እንደ መዳብ (ኮፐር)፣ ብረት (አይረን) እና ዚንክ ያሉ ንጥረ ነገሮች እና ቫይታሚን ኤ እና ቢ የያዙ ምግቦች ለፀጉራችን እድገት እና ጤንነት ወሳኝ ናቸው።

 

ፀጉራችን እነዚህን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ሲያጣም ቀለሙን መቀየር ይጀምራል።

ታዲያ አንዳንዶቻችን ይህን ያለ ጊዜው የመጣ ሽበት ለመከላከል የተለያዩ የኬሚካል ይዘት ያላቸውን እንደ ሻምፑ፣ የፀጉር ማጥቆሪያ እና ማቅለሚያዎችን እንጠቀማለን።

 

እነዚህ ነገሮች ግን ኪሳችን ከመጉዳታቸው ባለፈ ጎጂ ኬሚካሎችን ስለሚይዙ ፀጉራችን እና ጭንቅላታችን ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ነው የሚባለው።

በመሆኑም በተፈጥሯዊ መንገድ ችግሩን መከላከል የተሻለ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ለዚህም በየቤታችን በቀላሉ የምናገኘው ድንች መፍትሄ ነው ተብሏል።

ድንች ውስጥ የምናገኘው ስታርች የፀጉራችን ተፈጥሯዊ ቀለሙን እንዲይዝ ይረዳል።

የድንች ልጣጭን በሚከተለው መንገድ ቢጠቀሙ ከሳምንታት ወይም ከወራት በኋላ ውጤቱን በጉልህ ይመለከቱታል ይላል ዘገባው።

 

የሚያስፈልጉ ነገሮች

አንድ ኩባያ የድንች ልጣጭ እና 2 ኩባያ ውሃ

 

አዘገጃጀት

የድንች ልጣጩን በተጠቀሰው የውሃ መጠን ለ5 ደቂቃ መቀቀል፣ ከዚያም በማቀዝቀዝ ቢጫ ቀለም እስከሚይዝ ድረስ ጠብቆ ውሃውን ማፍሰስ፣

 

አጠቃቀም

እንደተለመደው ፀጉራችን በሻምፑ ታጥበን የበሰለውን የድንች ልጣጭ ፀጉራችንን መቀባት፤ ከዚያም በጨርቅ ጠቅልለን ለ15 ደቂቃ ያህል መቆየት፤

በመጨረሻም በውሃ ሙልጭ አድርገን መታጠብ፤

የበሰለው የድንች ልጣጭ ፀጉራችንን ጥቁር ከማድረጉም በላይ ካለ እድሜ የሚከሰትን ሽበት ለመከላከል ያግዛል።

 

ምንጭ፦ http://neopress.in/

 

  

Related Topics