ሙላቱ አሥታትቄ በ1926 አመተ ምህረት በ ጅማ ከተማ ተወለዱ።

ሙላቱ አሥታትቄ

 

Image result for ሙላቱ አሥታትቄ

 

አርቲስቶች ታዋቂ ሰዎች ዘፈን

ሙላቱ አሥታትቄ በ1926 አመተ ምህረት በ ጅማ ከተማ ተወለዱ። በ17 አመታቸው ማለትም በ1943 የምህንድሥና ትምህርት እንዲያጠኑ ወደ እንግሊዝ ሃገር በቤተሠቦቻቸው ተላኩ። ሆኖም ግን ለቤተሠቦቻቸው ሣይናገሩ የሙዚቃ ትምህርትን ተምረው ተመረቁ። ከዚህ ጎን ለጎንም የፒያኖ መሣሪያ መጫወትን ቻሉ። የሙዚቃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ እዚያው ለንደን የሚገኝና ሜትሮ በመባል የሚታወቅ ክለብ ውሥጥ ተቀጥሬው መሥራት ጀመሩ። ከዚያም እዚያው ለንደን ውሥጥ በደቡብ አሜሪካዊው በኢድሞንዶ ሮስ በሚመራው ኦኬሥትራን በመቀላቀል ብዙ ልምድን እንዳካበቱ ይናገራሉ።

 

ከዚሁ የለንደን ትምህርትና የሥራ ጊዜ ቆይታ በሇላ ወደ አሜሪካ በመጏዝ በኒዮርክ (New York) እና ቦሥተን(Boston) ተጨማሪ የሙዚቃ ትምህርት በመማር እዚሁ አሜሪካን  ሃገር ውሥጥ የኢትዮጵያን፣ የደቡብ አሜሪካ እና የጃዝ ዘፈን አጨዋወት ሥልቶችን በአንድ ላይ በማቀናጀት ኢትዮ-ጃዝ በሚል ሥያሜ መሥራት ጀመሩ።  በ1960ዎቹ ይህን ልዩ ፈጠራቸውን ወደ ሃገራቸው በመውሠድ እነ መሃሙድ አህመድ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ አለማየሁ እሸቴ እና ከመሠሉ እውቅ ዘፋኞች ጋር በመተባበር ሙዚቃዎችን የማቀናበር ሥራዎችን ሠርተዋል። ሙላቱ ካሣተሟቸው ሥራዎች ውሥጥ የሚከተሉት በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።

- Maskaram Setaba

- Afro-Latin Soul, Volume 1 & 2

- Mulatu of Ethiopia

- Yekatit Ethio-Jazz

- Plays Ethio Jazz

- Ethio Jazz (Mulatu Astatke Featuring Fekade Amde Meskel

- From New York City to Addis Ababa: The Best of Mulatu Astatke

- Assiyo Bellema

- Sketches of Ethiopia

- Ethiopiques

 

 

ሙላቱ ከሃገራቸው ውጭ ከተለያዩ እውቅ ባንዶች እና ባለሙያውች ጋር አብሮ የመሥራት አድሉን አግኝተዋል። ከነዚህም ውሥጥ ሎስ አንጀለሥ ውሥጥ ታዋቂ ከሆኑት የጃዝ ሙዚቀኞች ከነ Bennie Maupin, Asar Lawrence, Phil Ranelin ጋር በፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 2009 የሠሩት ተጠቃሽ ነው። 

ምንጭ፡-ሰዋሰዉ

 

  

Related Topics