የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል

የደም ማነስ ምልክቶች Symptoms of Anemia

 

 

 

የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው፣ የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር(ክንታሮት፣ ቁስለት፣ የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር የመሳሰሉት) አስተዋጽዎ ያደርጋሉ። ያለብዎት የደም ማነስ ቀለል ያለ ከሆነ ወይም ከብዙ ጊዜ በፊት ከተከሰተ ምንም አይነት ምልክት ላናይ እንችላለን። ለማንኛውም አይነት የደም ማነስ የጋራ የሆኑ ምልክቶች እነሆ

— የድካም ስሜት እና ጉልበት ማጣት

— ያልተለመደ ፈጣን የልብ ምት በተለይ እንቅስቃሴ ስናደርግ

— የትንፋሽ ማጠር እና ራስ ምታት

— የትኩረት ማጣት

— የማዞር ስሜት

— የቆዳ መገርጣት

— የእግር ጡንቻ መሸማቀቅ

— የእንቅልፍ ማጣት

1. በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ

በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩባቸው ይችላል

— ባልተለመደ ሁኔታ ወረቀት፣ በረድና ቆሻሻዎችን ለመመገብ መፈለግ

— ጥፍሮቻችን ወደላይ መታጠፍ(መበላሸት)

— የአፍ መሰነጣጠቅ እና መቁሰል

2. በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ

በቫይታሚን ቢ 12 እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ የሚከተሉት ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል

— በእጅና እግር ላይ መርፌ የመወጋት ስሜት መሰማት

— የመዳሰስ ስሜት ማጣት

— መንቀጥቀጥ እና ለመራመድ መቸገር

— የእጅና እግር መንቀርፈፍ እና መጠንከር(መገተር)

— የአስተሳሰብ መለዋወጥ

3. በሊድ(lead) መመረዝ የሚከሰት የደም ማነስ

በከባድ ሁኔታ በሊድ መመረዝ ወደሚከተሉት ምልክቶች ያመራናል

— ሰማያዊ_ጥቁር መስመር በድድ ላይ መኖር

— የሆድ ህመም

— የሆድ ድርቀት

— ማስታወክ

4. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት የሚከሰት የደም ማነስ

— የአይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን

— ቡናማ ወይም ቀይ ሽንት

— የእግር ቁስለት

— ህፃናት እንዳይፋፉ/እንዳይዳብሩ መሆን

— የኩላሊት ጠጠር በሽታ አይነት ምልክቶች

5. ሲክል ሴል የደም ማነስ

የሲክል ሴል የደም ማነስ ምልክቶች

— የድካም ስሜት

— ለኢንፌክሽን መጋለጥ

— በህፃናት ላይ የዕድገት እና ብስለት መዘግየት

— የመገጣጠሚያ፣ ሆድ፣ እጅና እግር በተወሰነ ቆይታ በተደጋጋሚ ከባድ የህመም ስሜት መከሰት ናቸው

 

የደም ማነስ ህክምና

የደም ማነስ ህክምና እንደመነሻው ይወሰናል

1. በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ

ይህ አይነት የደም ማነስ የአመጋገብ ስርዓታችንን እና ብረት በመውሰድ ማከም ይቻላል። ይህ የብረት እጥረት የተከሰተው ከወር አበባ ውጪ በሆነ የደም መፍሰስ ከሆነ የሚፈስበትን ቦታ ማወቅ እና እንዲቆም ማድረግ ተገቢ ነው።

2. በቫይታሚን እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ

ፎሊክ አሲድ እና ቫይታሚን ሲ እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ በምግብ መስተካከል ይችላል ስለዚህ በምግብዎ ውስጥ እነዚህን መጨመር ተገቢ ነው። ጨጔራችን ቫይታሚን ቢ 12 የመምጠጥ ችግር ካለበት በመርፌ መውሰድ(መወጋት) ተገቢ ነው።

3. በከባድ በሽታ የሚከሰት የደም ማነስ

የዚህ አይነቱ የደም ማነስ የተለየ ህክምና የለውም የጤና ባለሙያዎች ያለብንን ከባድ በሽታ ማከም ላይ ያተኩራሉ። ምልክቶቹ እየጨመሩ የሚመጡ ከሆነ የደም ልገሳና ቀይ የደም ሴሎች እንዲመረቱ የሚያደርግ ሆርሞን በመርፌ ይሰጣል።

4. አኘላስቲክ የደም ማነስ

ለዚህ ችግር ህክምና የሚሆነው የቀይ ደም ሴሎችን ቁጥር ለመጨመር የደም ልገሳ ነው። የአጥንት መቅኒ(bone marrow) ንቅለ ተከላ ሊደረግለት ይችላል።

5. በአጥንት መቅኒ ችግር የሚከሰት

የደም ማነስ

የዚህ በሽታ ህክምና ከቀላል መድሃኒቶች ጀምሮ ኬሞቴራፒ ወይም የአጥንት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል።

6. ሄሞላይቲክ የደም ማነስ

የዚህ ችግር ህክምና ችግሩን ሊያስከትሉ የሚችሉ መድሃኒቶች ካሉ ማቆም፣ ተያይዘው የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን ማከም፣ ቀይ የደም ሴሎችን የሚያጠቃ በሽታን የመከላከያ መንገዳችንን ለመግታት መድሃኒት መጠቀም ናቸው። እንዳለብን የደም ማነስ ህመም ክብደት/ጥንካሬ የደም ልገሳ እና የደም ማጣራት ህክምና ሊደረግለት ይችላል።

7. ሲክል ሴል የደም ማነስ

የዚህ አይነቱ የደም ማነስ ህክምና ኦክስጂን መስጠት፣ ህመም የሚያስታግሱ መድሃኒቶችን መውሰድ፣ በአፍና በደም ስራችን ፈሳሾች(fluid) መውሰድ ህመም ለመቀነስ ይረዳናል።

8. ታላሲሚያ የደም ማነስ

ይህ የደም ማነስ በደም ልገሳ፣ ፎሊክ አሲድ መውሰድ፣ ጣፊያን ማስወገድ፣ የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ማድረግ ለማከም ይረዳናል።

የአጥንት ጥንካሬ የሚሰርቁ  ምግቦች

ልብ ሳንል በምግብ ጉዳት ከሚደርስባቸዉ የሰዉነት ክፍሎች ውስጥ አጥንት አንደኛዉ ነዉ፡፡ አጥንት ጥንካሬ

ምንጭ፡-Danieltechnologist

 

  

Related Topics