የመዳፍ መስመርዎ ስለፍቅር ግንኙነት ህይወትዎ እንደሚናገር ያውቃሉ?

የመዳፍ መስመርዎ ስለፍቅር ግንኙነት ህይወትዎ እንደሚናገር ያውቃሉ?

 

 

በተለምዶ የልብ መስመር የሚሰኘው የመዳፍ መስመር ስለፍቅር ግንኙነት ህይወትዎ እንደሚናገር ያውቃሉ?

ይህ የመዳፍ መስመር ስለስሜትዎ እና አጠቃላይ የፍቅር እና የግንኙነት ህይወትዎ ይናገራል ይለናል የኸልዚ ፉድ ቲም ዶት ኮም ዘገባ።

በመሆኑም ሲያፈቅሩም ሆነ ሲፈቀሩ በምስሉ ላይ የተመለከቱት የመዳፍ መስመሮች ምን ያህል ከእርስዎ የመዳፍ መስመሮች ጋር ተቀራራቢ እንደሆኑ በማጤን ግንኙነትዎን ሊያሳምሩ ይገባል ሲልም ይመክራል።

ምስል “A”

በምስል “A” ላይ እንደተመለከተው የፍቅር መስመርዎ ከመሃል ጣትዎ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚነሳ ከሆነ እርስዎ መሪ ለመሆን ተፈጥረዋል ማለት ነው።

እርስዎ ለማወቅ ጉጉ እና በብዙ አቅጣጫ እራስዎን መቻልን የሚመርጡ፣ አስተዋይ፣ የውሳኔ ሰው ነዎት ይላል።

በአንፃሩ ረጋ ያሉ ሲሆኑ ፥ ብዙዎችን የሚስጨንቃቸው ጉዳይም እርስዎን ብዙ ሲያስጨንቅዎት አይታይም ።

ምስል “B”

በምስል “B” ላይ እንደሚታየው የፍቅር መስመርዎ የመሃል ጣትዎ እና የአመልካች ጣትዎ መጋጠሚያ ጋር የሚጀምር ከሆነ፥ እርስዎ ታማኝ እና ለሰዎች አክብሮትን በማሳየት ይታወቃሉ።

ውሳኔን በተመለከተ የመወላወል አይነት ባህሪን የሚያንፀባርቁ ቢሆንም የእርስዎን ታማኝነት በሚጠይቁ ሁኔታዎች ዙሪያ ግን ታማኝ ነዎት ይላል መረጃው።

ተግባቢ እና ጥንቁቅ መሆንዎም ተጠቁሟል።

ምስል “C”

በምስል “C” ላይ እንደተመለከተው መስመሩ ከአመልካች ጣትዎ መሃል ላይ የሚጀምር ከሆነ ደግሞ በምስል “A” ላይ የተጠቀሰው ግለሰብ አይነት ባህርይን ተላብሰዋል ይልዎታል።

ምስል “D”

በምስል “D” ላይ እንደተገለፀው የፍቅር መስመርዎ ወደታች በመቀልበስ በአመልካች ጣትዎ እና በአውራ ጣትዎ መካከል  ከጀመረ ግን እርስዎ ታጋሽ፣ ሰዎችን በመንከባከብ ደስታን የሚያገኙ፣ ቶሎ ሆድ የሚብስዎ ሆደ ቡቡ የሚባለው አይነት ስብዕናን ተላብሰዋል ማለት ነው።

እያንዳንዷን ነገር በዓላማ እና ለአላማ  ማከናዋን ደግሞ ይበልጥ የእርስዎን ማንነት የሚገልፁ ባህርያት ናቸው።

ምንጭ፦ http://www.healthyfoodteam.com

 

  

Related Topics