የአጥንት ጤንነትን ለመጠበቅ የሚሰጡ ምክሮች

የአጥንት ጤንነትን ለመጠበቅ የሚሰጡ ምክሮች

 

Image result for human bone structure

 

አጥንቶች ለሰዉነታችን ከሚሰጧቸዉ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ዉስጥ የተወሰኑት ለሰዉነታችን ቅርፅ ለመስጠት፣ የሰዉነት አካላትን ከአደጋ ለመከላከል፣ ስጋና ጡነቻዎቻችንን አጣብቆ ለመያዝና የካልስየም ንጥረ ነገርን ለማጠራቀም ይረዳል፡፡

ምንም እንኳ የአጥንትን ጤንነት ለመገንባት በልጅነታችንና በወጣትነት እድሜ ብዙ ነገሮችን ማድረግ የሚገባ ቢሆንም የአጥንት ጤንነትዎን ለመጠበቅ በአዋቂነት እድሜዎም አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ ይቻላል፡፡

የአጥንት ጤንነትዎን ሊወስኑ የሚችሉ ነገሮች ምን ምን ናቸዉ?

• በምግብዎ ዉስጥ የሚወስዱት የካልሲየም መጠን፡- በካልሲየም ንጥረ ነገር ያልበለፀጉ ምግቦችን አዘዉትሮ መዉሰድ ለአጥንት መሳሳት ከማጋለጡም በላይ አጥንት በቀላሉ እንዲሰባር ያደርጋል

• አካላዊ እንቅስቃሴ፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ/ ከማይንቀሳቀሱ ሰዎች ይልቅ ለአጥንት መሳሳት በከፍተና ሁኔታ ይጋለጣሉ

• ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጣት፡- ሲጋራ ለአጥንት ጥንካሬ መቀነስ የሚያጋልጥ ሲሆን፥ በየቀኑ ሁለትና ከዚያ በላይ አልኮል የሚወስዱ ደግሞ ለአጥንት መሳሳት ይጋለጣሉ፡፡

• ፆታ፣የሰዉነት መጠንና እድሜ፡-

• ዘርና በቤተሰብ ዉስጥ የአጥንት ችግር መኖር

• የሆርሞን መጠን፡- የታይሮይድ ሆርሞን መጠን ከፍ ሲል፣ ሴቶች በሚያርጡበት ወቅት፣ በወንዶች የቴስትሮን ሆርሞን መጠን መቀነስ ለአጥንት መሳሳት ይዳርጋሉ፡፡

• የአመጋገብ ስርዓት ችግር ያለባቸዉ ሰዎችና ሌሎች ሁኔታዎች፡- ለምሳሌ አኖሬክሲያ ነርቮሳ፣ የጨጓራ ቀዶ ጥገና፣ ክብደት ለመቀነስ የሚደረጉ ቀዶ ጥገናዎችና ሌሎች ነገሮች

• የተወሰኑ መድሃኒቶች፡- ለምሳሌ ኮርቲኮስቴሮይዶች (ፕሮዴኒሰሎን፣ ኮርቲሶን፣ ፕሪደንሶን፣ዴክታሜታሶን)፣ የተወሰኑ የጨጓራ መድሃኒቶች፣ የሚጥል በሽታ መድሃኒት

 

የአጥንትዎን ጤንነት ለመጠበቅ ማድረግ የሚገባዎ ነገሮች

• በምግብዎ ዉስጥ በቂ የካልሲየም መጠን እንዲኖር ማድረግ

• ቫይታሚን “ዲ”ን በአግባቡ ማግኘት

• በቀንተቀን ልማድዎ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማካተት

• እንደ ሲጋራ ያሉ ጎጂ ከሆኑ ዕፆችና እንዲሁም መጠጦችን ከመጠቀም መቆጠብ

ምንጭ፡ ሄሎ ዶክተር

 

  

Related Topics