የኩላሊት ጠጠሮች ጠጣር የሆኑ ትናንሽ ዝቃቾች ሲሆኑ የተሰሩትም ከሚኒራል

የኩላሊት ጠጠር ( KIDNEY STONES)

 

Image result for kidney stones pain

የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

የኩላሊት ጠጠሮች ጠጣር የሆኑ ትናንሽ ዝቃቾች ሲሆኑ የተሰሩትም ከሚኒራል እና ከአሲድ ሶልት ነው፡፡ የኩላሊት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ መስመር ማለትም ከኩላሊት እስከ ፊኛ ድረስ የማጥቃት ባሕሪም አላቸው፡፡

የኩላሊት ጠጠር ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ መቆየት የሚችል ሲሆን ከኩላሊት ተነስቶ በሽንት ማስወገጃ መስመር እስከ ፊኛ ድረስ ሊያደርግ በሚችለው ጉዞ ምክንያት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

 

✔ የኩላሊት ጠጠር ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• ከፍተኛ የጎን የሕመም ስሜት እና ከጎድን አጥንት በታች የጀርባ ሕመም ስሜት

• ከፍተኛ የሕመም ስሜት ወደ ንፍፊትና ወደ ታችኛው የሆድ ክፍል የሚሰራጭ

• የውኃ ሽንትን በምናስወግድበት ወቅት የሚኖር ከፍተኛ የሕመም ስሜት

• የውኃ ሽንት ቀለም ለውጥ(ቀይ፣ቡኒ ወይንም ሮዝ)

• የደፈረሰ ወይንም መጥፎ ጠረን ያለው የውኃ ሽንት

• አጣዳፊ የውኃ ሽንት መኖር

• የውኃ ሽንት ከሌላው ጊዜ በተለየ መብዛት

• ተያያዥ የሆነ ኢንፌክሽን የሚኖር ከሆነ ለምሳሌ ትኩሳትን ብርድ ብርድ ማለት መኖር

• በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰት ሕመም ቦታውን ሊቀያይር ይችላል፡፡ይህም የሚሆነው ጠጠሩ በሽንት ቧንቧ መስመር ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነው፡፡

✔ ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

ከታች የተጠቀሱትን የሕመም ምልክቶች ከተመለከቱ ወደ ሐኪም በአፋጣኝ መሄድ የኖርብዎታል፡፡ እነዚህም፡–

• ከፍተኛ የሕመም ስሜት የሚሰማዎ ከሆነ

• ከፍተኛ የሕመም (የውጋት) ስሜት

• ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ካለ

• ትኩሳትና ብርድ ብርድ ስሜት ካለዎት

• ደም የቀላቀለ የውኃ ሽንት ሲኖር

• የውኃ ሽንት ማስወገድ ካቃተዎ

✔ ለኩላሊት ጠጠር ሕመም ተጋላጭንት የሚዳርጉ ሁኔታዎች

• ጎልማሳ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ከ40 ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ ሰዎችን ያጠቃል

• ወንድ ፆታ ለኩላሊት ጠጠር ሕመም ተጋላጭነትን ይጨምራል

• የአመጋገብ ሁኔታችን ለምሳሌ ከፍተኛ መጠን ያለው የፕሮቲን፣ ጨው እና ስኳር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭነትን ይጨምራል

• በቂ የፈሳሽ መጠን አለመውሰድ ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡

• የሰውነት ክብደት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ከሆነ እና የመሳሰሉት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ፡፡

✔ የኩላሊት ጠጠርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

• በቀን ውስጥ የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን ይጨምሩ፡፡ የሚያስወግዱት የውኃ ሽንት መጠንም 2.5 ሊትር እንዲሆን ይመከራል፡፡

• የአመጋገብ ልምድዎን መቀየር የጨው መጠን እና የፕሮቲን መጠናቸው የበዛ ምግቦችን ማስወገድ ናቸው፡፡

✔ የኩላሊት ጠጠር ሕክምና ምንድን ነው?

የኩላሊት ጠጠር ሕክምና እንደጠጠሩ ዓይነት እና መጠን ይለያያል፡፡ የጠጠሩ መጠን አነስተኛ ከሆነ የቀዶ ጥገና ሕክምና አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡

• በቂ ፈሳሽ በመውሰድ (3 ሊትር) በቀን መውሰድ ጠጠሩ ከውኃ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ እንዲወጣ ይረዳል፡፡

• ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ አነስተኛ ጠጠሮች ስለሚያስከትሉ ሕም ማስታገሻ መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ 

• ሐኪምዎ ጡንቻዎችን የሚያፍታታ መድኃኒትም በመስጠት ጠጠሩ ከውኃ ሽንት ጋር ተቀላቅሎ እንዲወጣ እንዲረዳዎ ሊያደርግ ይችላል፡፡

• የጠጠሩ መጠን ትልቅ ከሆነ ሐኪምዎ የተለያዩ ጠጠሩን የማስወገጃ መንገዶችን የሚያማክርዎ እና የሚያስረዳዎ ይሆናል፡፡ ስለዚህም ሐኪምዎን በሚገባ ማማከር ተገቢ ነው፡፡

 

ምንጭ፡- ዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር

 

  

Related Topics