የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት

        የጉሮሮ ሕመም

 

Image result for የጉሮሮ ሕመም

 

የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡

የጉሮሮ ሕመም በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ቫይረስና ባክቴሪያዎች በአፍና በአፍንጫችን አድርገው በመግባትም ጭምር የጉሮሮ ሕመምን ያስከትላሉ፡፡

 

► የጉሮሮ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

✔ የጉሮሮ መከርከር

✔ ለመዋጥ መቸገር

✔ ትኩሳት

✔ ሳል

✔ የራስ ምታት

✔ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

✔ የድካም ስሜት መሰማት

✔ ብርድ ብርድ ማለት

✔ በጆሮና ባንገት አካባቢ ሕመም መሰማት

 

► በአንዳንድ ሰዎች ላይ ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጨማሪ

✔ ማቅለሽለሽ

✔ ማስመለስ

✔ መጥፎ የአፍ ጠረን

✔ የድምፅ መለወጥ

✔ አፍን ለመክፈት መቸገር ሊኖሩ ይችላል

የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ሕመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት

ይለያያል፡፡ በቫይረስ ምክንያት የሚመጣን የጉሮሮ ሕመም ሰውነታችን ባለው የበሽታ መከላከል አቅም የሚዋጋ ሲሆን መድኃኒት መውሰድ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰትን የጉሮሮ ሕመም ሕክምና ቦታ በመሄድ ባክቴሪያ አጥፊ መድኃኒቶችን (Antibiotics) መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

 

► ከዚህ በተጨማሪ የሕመሙን ሁኔታ እንዲያስታግስልን፤

✔ በቂ ዕረፍት መውሰድ

✔ ትኩስ ፈሳሽ መውሰድ፡- ሻይ፤ወተት፤አጥሚት

✔ ለስለስ ያሉ ምግቦችን መመገብ፡- ሾርባ

✔ ለብ ባለ ውሃ በጨው እና በዝንጅብል መጉመጥመጥ

✔ ሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡

 

ምንጭ :  ኢትዮ ጤና ፌስቡክ

 

  

Related Topics