የኤንተርኔት ትዳር አባት የሚል ስያሜ በተሰጣቸዉ ኒል ክላርክ ዋረን በተባ

ትዳር በኢንተርኔት

 

በአለማችን የደረሰዉ የገንዘብ ቀውስ የአለም ንግድ ልውውጥን ለከፍተኛ ኪሳራ በመዳረግ ብዙ ኢንዱስትሪዎች እንዲዘጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከስራ እንዲፈናቀሉ በማደረግ የማዕበሉ ወላፈን ያልገረፈዉ የንግድ ዘርፍ ባይኖርም ከገመቱዉ በላይ ደንበኞቻችን በማፍራት ከግማሽ ሚሊየን ዶላር የበለጠ ትርፍ ያስመዘገበዉ በካሊፎርኒያ ፓሳዴና የሚገኘዉ ‹‹ ኢ-ሀርመኒ›› የተባለዉ ኢንተርኔት ጥንዶች እያገናኘ ጎጆ እንዲቀልሱ ትዳር እንዲመሰርቱ የሚያደርገዉ ‹‹ማች ሜኪንግ›› የተባለዉ ካንፓኒ ነዉ፡፡

የኤንተርኔት ትዳር አባት የሚል ስያሜ በተሰጣቸዉ ኒል ክላርክ ዋረን በተባሉት የስነ ልቦና ምሁር መስራችነት እ.ኤ.አ በ200 ኢ-ሀርመኒ (e- Harmony) በሚል ስያሜ ለትዳር ፈላጊዎች 436 ጥያቄዎች በማቅረብ ፍላጎታቸዉ የሚቀራረብ ትዳር ጠያቂዎችን በድህረ ገጽ ተገናኝተዉ እንዲወያዩና ዉል እንዲፈራረሙ በማድረግ ስራዉን ጀመረ ክላርክ ዋረን በካሊፎርኒያ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ አስገብተዉ ትዳር የሌላቸዉ በማቀራረብ ትዳር እና ፍቅር እንዲመሰርቱ ለማበረታታት ስራዉን ሲጀምሩ ዋናዉ ግባቸዉ በአሜሪካ እድሜያቸዉ ከ18 ኣመት በላይ የሆኑ ከጠቅላላዉ ህዝብ አንድ ሶስተኛ እጅ ያላቸዉን 92 ሚሊዮን  ህዝብ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ይሁንና ስራዉ እንዲጀመር ድህረ ገጻቸዉ አመት ሳይሞላዉ በአንድ አመት ውስጥ 16 ሚሊየን አሜሪካዊ በ35 ዶላር ወርሀዊ ክፍያ እየከፈሉ በድርጅቱ በኩል የሚመጥናቸዉንና መስፈርታቸዉን የሚያሟሉ ጎልማሳ እና ኮረዳ መምረጥ ሲጀምር ያልጠበቁት እና መና ሲበዛላቸዉ ፊታቸዉ ከአሜሪካ ዉጪ በ35 ሀገራት በተለይም የህዝብ ብዛት ባላቸዉ በህንድ እና በቻይና አንድ ሺህ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈት ከኪሳራ  የጸዳዉ (re-cession-proof) የኢንተርኔት ትዳር በየአመቱ ከሁለት ትዳር በየአመቱ ከሁለት ቢሊየን ዶላር ገቢ እያፈሱ ነዉ፡፡ በየቀኑ ከ 90 የሚበልጡ ትዳር ፈላጊዎች ፍቅርና ትዳር በሚመሰርቱበት በየአመቱ ‹‹ሀርመኒ›› የተባለ ስም የተሰጣቸዉ 100 ሺህ ልጆች እንዲወልድ መንገድ በከፈተዉ የአሜሪካዉ ኢ-ሀርመኒና እና ያሆ ብቻ በ2006 ከደንበኞች ወርሃዊ ክፍያ ወደ ካዝናቸዉ ያስገቡት 649 ሚሊየን ዶራል እንደሆነ ከአሜሪካ ፌድራል ገቢዎች የወጣዉ አመታዊ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡

በኢንትርኔት ትዳ ፈላጊዎች የፊት ገጽታና የጭንቅላት ቅርጽ ከባህሪ ጋር ያለዉ ዝምድና

በኢንተርኔት ትዳር ፈላጊዎች ከፎቶአቸዉ የሚገኙ መረጃ ባህሪያቸዉ የሚተነተነዉ የፊት ገጽታ ከባህሪ ጋር ያለዉን ዝምድና የሚያጠናዉ ፊዚዮግኖሚ ‹‹physiognomy>> በተባለዉ ሳይንሳዊ መላ ምት ነዉ፡፡

የዘርፉ ተመራማሪዎች የሰዉ ልጅ ምክንያቱም ሊያዉቀዉ ባይችልም የእከሌ አይን ትናንሽ  ሆነዉ የተጠጋጉ መሆናቸዉን ሳይ ገና ሳይነግሩኝ አጭበርባሪ መሆኑን አዉቄያለዉ፡፡ የእከሌ ግንባር ወጣ ማለቱ ጠልቆ የማሰብ ብቃቱን የሚያሳይ ነዉ ሲል ይደመጣል፡፡ ይህ አገላለጻቸዉ እንደ ተራ ነገር አዳምጠነዉ ብናልፍም ጠልቀን ስንመረምርዉ ከእዉነታ ጋር የተዛመደ ነዉ ይላሉ፡፡

ከዚሁ የመጀመሪያ የባህሪ መለያ መስፈርት አጠቃላይ እና ፈጣን መረጃ የሚጠቀመዉ የፊት አጠቃላይ ዉጫዊ ገጽታን በመመልከት የምናገኘዉ መረጃ ነዉ፡፡ በሶስት ምድብ በተከፈተዉ በዚህ ባህሪ መለያ መገለጫ መሰረት

አንደኛዉ የግማሽ ክብ ውጫዊ ገጽታ (ኮንቬክስ) ቅርስ የያዘ የፊት ገጽታ ያለዉ ይኸዉም ወጣ ያለ አፍንጫ ከቦታዉ ወደ ኋላ ተዳፉት የስራ ግንባርና ወደ ኋላ የሸሸ አገጭ የያዘ ፊት ያለዉ ግለሰብ ስሜቱን በመግለጽ በአነጋገር በድርጊት አንዳንድ ግዜ ድፍረት የሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች ወደ ድርጊት አንዳንድ ግዜ ድፍረት በሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች ወደ ድርጊት እንዲገባ አስተዋጾ የሚያበረክት ፊት ለፊት የሚያጋፍጠን ተሟጋቾች ነዉ፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ ለአዳዲስ ንድፈ ሀሳቦች ራሱን በፍጥነት የሚያዘጋጅ አስቂኝና ጨዋታ አዋቂ ጥሩ ወዳጅ ነገሮች በቀጥታና በቀናነት የሚመለከት አንዳንድ ግዜ አቀራረቡንሊያግባባ በሚችልበት መንገድ የሚለዉጥ ቢሆንም ትግስት በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ድክመት የሚስተዋልበት ነዉ፡፡

ከዚሁ አጠቃላይ የፊት ገጽታ የማንበቢያ ሳይንስ ሁለተኛዉ ኮንኬቭ የተባለዉ ከላይ የተገለጸዉ የፊት ገጽ አቀማመጥ በተቃራኒ  ቢወደ ውስጥ የሰረጎደ የሚመስል ግንባርና አገጭ በመጠኑ አነስተኛ የሆነ አፍንጫ ያለዉ ግለሰብ ይህ ግለሰብ ረጋ ያለ ዝምተኛና ታጋሽ ምንም ጉዳይ በችኮላ የማይፈጸም ጥንቁቅና አስተዋይ የሚባሉ በራሱ የሚተማመንና ዘዴኝነት የሚስተዋልበት ሲሆን ሀሳብ የማፍለቅ ችሎታዉ በተቃራኒዉ ደካማ የሚበል ነዉ፡፡

በሶስተኛ ምድብ የሚቀመጡት ከግንባሩ የላይኛዉ ጫፍ እስከ አፍንጫ ከአፍንጫዉ የላይኛዉ ክፍል መጀመሪያ ቀጥ ያለ ቀጥ ብሎ ወጣ አፍንጫ ከአፍንጫዉ የታችኛዉ ጫፍ ያለዉ ርዝመት ተመጣጣኝ ከሆነ ክብ ቅርጽ ያለዉ ወይም ኮንኬቭና ኮንቬክስ የተባሉት ከላይ አንደኛ በሁለተኛ የፊት ቅርጽ አቀማመጥ የተገለጹት  የፊት ገጽታች በጥምረት የያዘ ፊት ነዉ፡፡ ይህ ገጽታ ያለዉ ግለሰብ እንደአስፈላጊነቱ ወደ አደላዉ ክፍል የሚገለባበጥ በሁለት ተቃራኒ ጎራ ተመቻችቶ ለመቀመጥ የሚያስችላቸዉ መላ እየዘየደ የሚኖር ግለሰብ ነዉ፡፡

በኢንተርኔት ድርጅቶች ላጤዎችን ለማጋባት ያስችላል ብለዉ በመስፈርቱ  ካስቀመጡት መላምቶች ከላይ የጠቀስነዉን አጠቃላይ የባህሪይ መገለጫ አንዱ ቢሆንም ሰፊዉን ቦታ የሚሸፍነዉ ወደፊት ልናቀርበዉ የምንሞክረዉ አንዳንዱን የፊት አካል አይን ጆሮ ግንባር የአይን ቀለም ከንፈር ወዘተ በተመለከተ የቀረበዉ የባህሪ ትንታኔ መገለጫ ነዉ፡፡

ምንጭ፡- ያኔት መጽኄት ቅጽ2 ቁጥር 20 2002 ዓ.ም