ቀይ ስር - በቤት ውስጥ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር

ቀይ ስር - በቤት ውስጥ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር

 

 

የደም ግፊት ልባችን ደምን ወደ ተለያዩ ክፍሎች ለማሰራጨት ሲል በደም ቅዳ ቧንቧዎች ላይ የሚፈጥረው ግፊት ሲሆን፥  በእያንዳንዷ የልብ ምት መቀነስ እና መጨመር የሚወሰን ነው።

አቀማመጣችን፣ የምናደርገው እንቅስቃሴ፣ ጭንቀት አልያም እንቅልፍ ማጣትም የደም ግፊታችን መጠን የመቀያየር ሀይል አላቸው።

የአሜሪካ የልብ ማህበር እንደሚለው የጤናማ ሰው የደም ግፊት የሲስቶሊክ (የልብ ጡንቻ ሲኮማተር በደም ስሮች ውስጥ ያለውን ግፊት የሚገልፅ) እና ዳያስቶሊክ ቁጥሮች (በልብ ምቶች መካከል ያለውን የደም ግፊት የሚያሳይ) 120 እና 80 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ እና በዚያ መካከል ሲሆኑ ነው።

ስለሆነም 120 በ80 ሚ.ሜ ሜርኩሪ አካባቢ የሚነበብ የደም ግፊት አንድ ሰው ጤናማ የደም ግፊት አለው ያስብላል።

የደም ግፊት ተከሰተ የምንለው የሲሰቶሊክ ግፊት ከ140-150 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆን ወይም የዳያስቶሊክ ግፊት ከ90-99 ሚ.ሜ ሜርኩሪ ሲሆን ነው፡፡

የአሜሪካ የልብ ማህበር አንድ ሰው የደም ግፊት በሽታ አለበት ብሎ የሚያምነው ይህ ቁጥር ሰፊ በሆነ የጊዜ ክልል ውስጥ ሳይቀንስ ሲቆይ ነው፡፡

የደም ግፊት መጠናችን 160 በ100 ሚ.ሜ ሜርኩሪ እና ከዚያ በላይ ከሆነም ለከፍተኛ የደም ግፊት መጋለጥን የሚያሳይ ሲሆን፥ ክብደት መቀነስ፣ የተሻለ የአመጋገብ ስርአት መከተል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይመከራል።

ቀይ ስር መመገብም ከፍተኛ የደም ግፊት ችግርን ለማቃለል ሁነኛ ዘዴ ነው ተብሏል።

በየቀኑ ቀይ ስርን በጥሬው መመገብ አልያም አንድ ብርጭቆ የቀይ ስር ጭማቂ መጠጣት የደም ግፊትን ለመቆጣጠር እና ወደ ተለመደው ሁኔታ እንዲመለስ ያግዛል።

የደም ቧንቧዎች የመስፋት እና የመኮማተር አቅማቸውንም በ20 በመቶ እንደሚያሳድግ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ቀይ ስር በውስጡ የያዘው ናይትሬት በሰውነታችን ውስጥ ወደ ናይትሪክ አሲድ ይቀየራል። ይህም ከጥቂት ስአታት በኋላ የደም ግፊት መጠንን ይቆጣጠራል።

ምሳ ሰአት ላይ የቀይ ስር ሳላድ መመገብም በፍጥነት ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቀነስ እና የተስተካከለ የደም ግፊት ንባብ (ቁጥር) እንዲኖር ይረዳል።

ምንጭ፦ www.fitbodycenter.com/

 

 



 

Related Topics