የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች እስካሁን አለም ከደረሰባቸው የእርግዝና የአ

 

የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች (contraceptives)

 

የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች እስካሁን አለም ከደረሰባቸው የእርግዝና የአባላዘር መከላከያ መንገዶች ቀላሉ፣ ወጪ ቆጣቢና የተሻለ አማረጭ ናቸው።

የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች ተፈጥሯዊ(natural method)፣ የአካላዊ ግርዶሽ(barrier methods)፣ማህፀን ውስጥ የሚገቡ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች (intrauterine contraceptive devices)፣ሆርሞናል የወልድ መቆጣጠሪያዎች (hormonal methods) እና ዘለቀታዊ ወልድ መቆጣጠሪያዎችን (permanent methods) ያካትታል። ሆርሞናል የወሊድ መቆጣጠሪያዎችም በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ እስካሁን ግንባር ቀደምና ተመራጩ መንገድ ነው።

ብዙውን ጊዜ ተጠቃሚዎች ከኑሮ ብሂላቸውና እምነታቸው ጋር የሚመቻቸውን እንዲጠቀሙ የሚበረታቱ ሲሆን የተሻለ ውጤት እንዳላቸውም ጥናቶች ያስረዳሉ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትም ነጥቦች ለወልድ መከላከኛ ምርጫው በይበልጥ ይረዳሉ፦

-ውጤታማነት(efficacy) -ላጠቃቀም አመቺነት(convenience) -መከላከያው የሚቆይበት የጊዜ እርዝማኔ(duration of action) -ዳግም የወልድ እድል የማግኘት እድል -ከወሊድ መከላከኛ ዜዴው ጋር የሚመጣ የማህፀን ደም መፍሰስ -የጎንዮሽ ጉዳት(side effect) መጠን -የዋጋው ተመጣጣኝነት(affordability) -ከአባላዘር በሽታ የመከላከል አቅም -ሌሎች መከላከያ መንገዱን ሊከለክሉ የሚችሉ ሁኔታዎች(medical contraindication)

ተገቢ የሆነውንና ለራስ በሚስማማ መንገድ የወልድ መቆጣጠሪያን መጠቀም እንግዲህ ብልህነት ነው እንላለን፤እዚህ ላይ የዝግጅት ክፍላችን ማሳሰብ የሚፈልገው የወልድ መቆጣጠር ስራ የወንዱ ድርሻም እንደሆነ ነው።

ምንጭ፡-.ethiohakim

 

  

Related Topics