በጣም መክሳትም ሆነ አብዝቶ መወፈር ሁለት የተለያዩ ግን ደግሞ የማይጣጣሙ

በጣም መክሳትም ሆነ አብዝቶ መወፈር ሁለት የተለያዩ ግን ደግሞ የማይጣጣሙ ፍላጎቶች ናቸው።

 

 የሰውነት ክብደትን የሚጨምሩ የማለዳ ልማዶች

 

ባለሙያዎችም በልክ የሆነ ውፍረት እና የተስተካከለ አቋም እና ሰውነት መልካም መሆኑን አበክረው ይመክራሉ።

ሰውነት ለመቀነስ በሚል የሚወሰን ውሳኔ እና ተቃራኒውን ለማድረግ በሚል የሚወሰድ መፍትሄ አንዳንድ ጊዜ ተቃራኒውን ውጤት ሲያመጡም ይስተዋላል።

ባለሙያዎች ደግሞ ሳይታወቁ የሚከወኑና የሰውነት ክብደት እንዲጨምር የሚያደርጉ የማለዳ ልማዶችን ይጠቅሳሉ።

እንደ እነርሱ ገለጻ ሳይታሰብም ይሁን እያወቅነው የሚደረግ ግን ደግሞ ለሰውነት ክብደት መጨመር አይነተኛ ሚና ያላቸው ልማዶች አሉ፤

አብዝቶ መተኛት፦ ቀንም ሆነ ማታ ለመተኛት በሚደረግ ሙከራ ውስጥ በአግባቡ አለመተኛት እና የእንቅልፍ መቆራረጥ ለውፍረት የመዳረግ እድል እንዳለው ይነገራል።

ይሁን እንጅ ከተለመደው በላይ ከልክ ያለፈ ሰዓት መተኛትም ለሰውነት ክብደት መጨመር የራሱ አስተዋጽኦ አለው።

ለዚህ ደግሞ ከተለመደው የ7 እና 8 ሰዓት መኝታ በበለጠ መተኛት ለዚህ ችግር መዳረጉን በቅርብ ጥናታችን አይተናል ይላሉ ባለሙያዎቹ።

ስለዚህም አብዝታችሁ ባለመተኛት የሰውነት ቅርጻችሁንም ሆነ ጤንነታችሁን ጠብቁ በማለት ይመክራሉ።

ማለዳ በጨለማ ክፍል ውስጥ ማሳለፍ፦ ሌላው ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ ማለዳ ከእንቅልፍ ሲነቁ ከአልጋ ወደ ስራ በማምራት ሰውነት የሚፈልገውን የፀሃይ ብርሃን መንፈግ ነው።

አብዛኞቹ ሰዎች ከእንቅልፍ እንደነቁ ቀጥታ ወደ ስራ በማምራት ፀሃይ የማያገኙበትን የጨለማ መሰል ውሎን ይመርጣሉ።

ይህ መሆኑ ግን ጉዳት አለው፥ ከቪታሚን ዲ ባለፈ ሰውነታችን ማለዳ ሰብስቦ ለስርዓተ ምግብ መፈጨት የሚጠቀምበትን ሂደት ያሳጣዋል።

ይህ ደግሞ ከሚመገቡት ምግብ ጋር ተዳምሮ ለአላስፈላጊ ውፍረት ይዳርጋልና ከዚህ መሰል ልማድ ይራቁ።

ብርሃን የሚፈነጥቅ ቀንን እያዩ ማሳለፍና ለስራ ሲባል፥ ገና በማለዳ ጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻ ማሳለፉ የራሱ ተፅዕኖ እንዳለውም ይጠቅሳሉ።

ያልተመጣጠነ ቁርስ፦ ቀን ላይ ለሚመገቡት ምግብ ወሳኙ ነገር ጠዋት የተመጣጠነ ቁርስን መመገብ ነው፤ ይህ ልማድ ቀን ላይ የሚመገቡትን ምግብ በአግባቡ ለመወሰን ይረዳል ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች።

እንደ እነርሱ ገለጻ ማለዳ ላይ ያልተመጣጠነ እና በተዛባ መልኩ የሚወሰድ ቁርስ ቀን ላይ የአመጋገብ ስርዓትን የማዛባት አቅም አለው።

ይህ ደግሞ የተቆራረጠ እና ያልተስተካከለ አመጋገብን በማስከተል፥ ከልክ በላይ እንዲመገቡ በማድረግ አላስፈላጊ ውፍረትን ያስከትላል።

እናም ማለዳ በተቻለ መጠን የተመጣጠነ ቁርስን ተመግበው ይውጡና የሰውነት ክብደትዎን ይጠብቁ ሲሉ መልዕክታቸውን ያደርሳሉ።

ማለዳ ስኳር አብዝቶ መጠቀም፦ ማለዳ ከቁርስ ጋር አልያም ከዛ በኋላ ረፋድ ላይ ሻይ ቡና ሲሉ ጣፋጭ እና ስኳር የሚያበዙ ከሆነም ለዚህ ችግር ይዳረጋሉ።

ይህ ልማድ በበርካቶች ዘንድ እንደ መዘውተሩ መጠን፥ ለሰውነት ክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው ያሉት።

እንደ ባለሙያዎች ገለጻ በቀን እስከ አምስት ሲኒ ቡና መጠጣት እና መጠቀም ለዚህ ችግር ይዳርጋልና የካሎሪን መጠን ከፍ ከሚያደርጉ አመጋገቦች መጠንቀቅ ይበጃል።

ይህን መሰሉ ልማድ ከውፍረት ባለፈ ለስኳር በሽታም ይዳርጋል።

ክትትል አለማድረግ፦ በየዕለቱ የሰውነት ክብደትን መከታተል ጥርስን እንደ መቦረሽ ሊለመድ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

የሰውነት ክብደትን መከታተል እና ማወቁ ክብደትን ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን የተስተካከለ አቋምን ለመያዝ እንደሚረዳም ይናገራሉ።

እናም በየጊዜው የሰውነት ክብደትን ለውጥ መከታተልና መገምገም ከሚፈጠር አላስፈላጊ የሰውነት ክብደት ለመራቅ ይረዳል።

 

ምንጭ፦ womenshealthmag.com

 

  

Related Topics