አልኮል መጠጣት የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን ሊጨምር ይችላል ተባለ

አልኮል መጠጣት የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን ሊጨምር ይችላል ተባለ

 

Related image

 

አልኮል መጠጣት የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ ተጋላጭነትን እንደሚጨምር የ27 የጥናት ውጤቶች ድምር አሳይቷል።

ከካናዳ እና ከአውስትራሊያ የተወጣጡ ተመራማሪዎች አልኮል እና የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዳለው ማረጋገጡን የገለጹ ሲሆን፥ ሆኖም ግን የፕሮስቴት ካንሰር አልኮልን በመጠጣት ይመጣል ለሚለው ግን ማረጋገጫ አላገኘንም ብለዋል።

ሆኖም ግን አልኮልን በማንኛውም መጠን መጠጣት ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን ይጨምራል የሚለውን ተመራማሪዎቹ ያብራራሉ።

ለምሳሌ በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት መጠጥ የሚጠጣ ሰው ከማይጠጡት ጋር ሲነጻጸር ከ8 እስከ 23 በመቶ ለፕሮስቴት ካንሰር የተጋለጠ ነው ተብሏል።

አዲሱ የጥናት ውጤትም አልኮልን በመጠጣት እና በፕሮስቴት ካንሰር መካከል ግንኙነት እንዳለ የሚያሳይ ነው ሲሉም ተመራማሪዎቹ ይነገራሉ።

በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኑ አስተባባሪ የሆኑት ቲም ስኮትዌል፥ በአልኮል ለፕሮስቴት ካንሰር መስፋፋት የሚያደርገው ተፅእኖ ወደ ፊት የሚያመጣውን መዘዝ መገመት አያዳግትም፤ በዚህ ከቀጠለ ደግሞ የፕሮስቴት ካንሰር ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑ አይቀሬ ነው ብለዋል።

የጥናት ቡድኑ ተባባሪ የሆኑት ታንያ ቺክሪቲዚዝ በበኩላቸው፥ የጥናቱ ግኝት በአልኮል እና በጤንነት ዙሪያ የሚደረገው ጥናት የተሻለ ስራ እንደሚፈልገው ያሳየ ነው ብለዋል።

የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ ወንዶችን ለሞት እየዳረጉ ካሉ የካንሰር አይነቶች ውስጥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል።

አልኮል የጡት ካንሰርን ጨምሮ ለሰባት አይነት የካንሰር ህመሞች መንስኤ እንደሆነም በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ከዚህ በተጨማሪም አልኮል ለቆዳ እና ለጣፊያ ካንሰር እንደሚያጋልጥም ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ።

 

ምንጭ፦ www.upi.com/Health

 

  

Related Topics