እንቁላልን መመገብ ለስትሮክ ተጋላጭነታችንን እንደሚቀንስ ጥናት አመል

 እንቁላልን መመገብ ለስትሮክ ተጋላጭነታችንን እንደሚቀንስ ጥናት አመልክቷል።

 

 

Image result for እንቁላል

 

በአሜሪካውያን ተመራማሪዎች ይፋ ባደረጉት ጥናት መሰረት፥ በቀን ውስጥ አንድ እንቁላል መመገብ የስትሮክ ተጋላጭነትን ይቀንሳል።

ከ33 ዓመት ቀደም ብሎ በወጣ የጥናት ውጤት ላይ በየእለቱ እንቁላለን መመገብ የደም መላሽ የልብ ቧንቧ /coronary/ የልብ ህመም ጋር ግንኙነት እንዳለው ያሳይ ነበር።

ተመራማሪዎች አሁን በሰሩት ጥናት ግን እንቁላልን መመገብ የደም መላሽ የልብ ቧንቧ /coronary/ የልብ ህመም ጋር ግንኙነት እንደሌለው አጣርተናል ነው የሚሉት።

ይህን ለማጣራትም የ275 ሺህ የጥናቱ ተሳታፊዎች ላይ ምርምር ማድረጋቸው ተገልጿል።

በጥናቱም የተሳታፊዎች እንቁላል መመገብ የደም መላሽ የልብ ቧንቧ /coronary/ የልብ ህመም እና ከስትሮክ መካከል ያለውን ገንኙነት ሲያጣሩ ቆይተዋል።

በአሜሪካ ኤፒድሳት ተቋም የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ዶሞኒክ አሌክሳንደር፥ የጥናቱ ዋና አላማ የሰዎች የእንቁላል አመጋገብ እና የስትሮክ ህመም መካከል ያለውን ግንኙነት ለመለየት ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን እንቁላል ለሰው ልጅ ጤና የሚበጁ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ለይተናል ይላሉ ዶክተር ዶሚኒክ።

ከዚህ በተጨማሪም እንቁላል ዋነኛው የፕሮቲን መገኛ ነው የሚሉት ዶክተሩ፥ ይህ ደግሞ የደም ግፊትን ለመቆጣጣር ይረዳል ነው የሚሉት።

አንድ እንቁላል 6 ግራም ከፍተኛ ጥራት ለው ፕሮቲን፣ አንቲ ኦክሲዳንት እንዲሁም ቪታሚን E፣ D እና A የበለፀገ ነው ይላሉ ተመራማሪዎቹ።

ስለዚህ በቀን አንድ እንቁላል መመገብ በርካታ የጤና እክሎችን ለመከላከል ይረዳል የሚሉት ተመራማሪዎቹ፥ በተለይም የስትሮክ ተጋላጭነታችንን በ12 በመቶ ይቀንሳል ይላሉ።

 

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk/health

 

 

 

  

Related Topics