አትሌት ደራርቱ ቱሉ (ኮሎኔል)

 

 

አትሌት ደራርቱ ቱሉ (ኮሎኔል) ማንናቸው?

 

 

 

አትሌት ደራርቱ ቱሉ (ኮሎኔል) ከኢትዮጰያም አልፎ በአለማቀፍ ደረጃ በረጅም ርቀት ተደናቂ ከሆኑት ሴት አትሊቶች አንዷ ነች፡፡ ኲሎኔል ደራርቱ አርሲ ውስጥ በቆጂ በተባለ አካባቢ በ1966 ዓ.ም. ተወለደች፡፡ ኮሎኔል ደራርቱ እስፓርታዊ ውድድር ማድረግ የጀመረችው ገና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ በነበረችበት ጊዜ እንደነበር ታሪኳ ያስረዳል፡፡ ደራርቱ  ወደ መጨረሻው የትምህርት ቤቷ የቆይታ ዘመን ትምህርት ቤቷን እየወከለች በ800  እና በ1500 ሜትር ርቀቶች እየተወዳደረች በተደጋጋሚ መልካም ውጤቶችን አስመዝግባለች:: በትምህርት ቤት ውድድሮች ታዋቂነትን እያገኘች ንደመጣች በ1980 ዓ.ም. የማረሚያ ቤቶች ስፓርት ክለብ አባል ሆነች:: በ1981 ዓ.ም. ኖርዌ ስታቬንጋር ከተማ ውስጥ በተካሄደው  17ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ በስድስት ኪሎ ሜትር የመጀመሪያውን አለም አቀፍውድድር በማድረግ 23ኛ ደረጃ መውጣቷ ይነገራል፡፡ በቀጣዬ ዓመት በተመሳሳይ ርቀት በፈረንሣይ አገር ተወዳድራ የአንደኛነት ደረጃን አገኘች::  በዚያው ዓመት ቡልጋሪያ ላይ በተካሄደው የ10000 ሜትር ውድድር አሁንም አንደኛ ሆነች:: ኮሎኔል ደራርቱ በ1984 ዓ.ም. በእስፔን ዋና ከተማ በባርሴሎና ተዘጋጅቶ በነበረው አሎምፒክ በ10000 ሜትር ተወዳድራ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት የወርቅ ሜጻሊያ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች፡፡

 

ይህን ድል አስመዝግባ ወደአገሯ አንደተመለሰችም በርኧሰ_ብሄሩ የሽለቅነት ማዕረግ አግኝታለች፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ኮሎኔል ደራርቱ በአለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ሜጸለያዎችን አግኝታለች፡፡ በ1993  በአውስትራሊያ ዋና ከተማ በሲድኒ ተደረገው የእሎምፒክ ውድድር በተለመደው የ10000 ሜትር ርቀት ተወጻድራ የወርቅ ሜዳለያ ተሸላሚ ሆናለች::

 

 

 

በኢትዮጵያም ሆነ በጥቁር አፍሪካ ኦሊምፒክ ታሪክ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ኲሎኔል ደራርቱ ቱሉ ሰኔ 2007 ዓ.ም.  ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብላለች፡፡

 

የኮሎኔል ደራርቱ ፈለግ በመከተል በ10000 እና በ5000 ርቀቶች ከፍተኛ ውጤት በማከመዝገብ ላይ ከሚገኙት ሴት አትሌቶች  መካከል ጊጤ ዋሚ፡ ጥሩነሽ ዲባባና መሰረት ደፋር ተጠቃሾች ናቸው፡፡

 

           ምንጭ፡-ሰዋሰዉ

 

  

Related Topics