ስለትርፍ አንጀት በሽታ

ትርፍ አንጀት (appendicitis)

እስቲ ዛሬ ስለትርፍ አንጀት በሽታ ጥቂት እንበላችው፡፡
ትርፍ አንጀት በቀኝ በታችኛው የሆድ ክፍል ትልቁ አንጀት ላይ ተቀጥላ
የምትገኝ ትንሽ አካል ናት፡፡
 የትርፍ አንጀት ሕመም በምን ይከሰታል?
የትርፍ አንጀት ሕመም የሚመጣው በትርፍ አንጀትና በትልቁ አንጀት መካከል የሚገኘው አንገት ሲዘጋ ነው፡፡ ይህ በሠገራ፤ በ ሆድ ውስጥ ትላትል ፣በቁስ አካል ወይንም በካንሰር አልያም በኢንፌክሽን ምክንያት ሊዘጋ ይችላል፡፡

 የትርፍ አንጀት ሕመም ምልክቶች
• ማቅለሽለሽና ማስመለስ
• ከእምብርት አካባቢ ጀምሮ ወደ ታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል የሚወርድ
የህመም ስሜት
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ትኩሳት
• አየር ለማስወጣት መቸገር
• ለመንቀሳቀስ መቸገር

 የትርፍ አንጀት ምርመራ ምንድነ ነው
• የቃልና አካላዊ ምርመራዎች
• የሆድ የቴሌቭዝን ምርመራ( abdominal ultrasound )
• የደምና የሸንት ምርመራ

 የትርፍ አንጀት ሕክምና ምንድን ነው?
ምንም ዓይነት ምግብ ወይንም መጠጥ ወይንም ሕመም ለማስታገስ
የሚወሰዱ የቤት ውስጥ መድኃኒቶች እንዳይወሰዱ ይመከራል፡፡ ይህም
ያበጠው ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ ያደርጋል፡፡
• በቀዶ ጥገና የትርፍ አንጀቱን ቆርጦ ማውጣት ይህም በህክምናዉ
(Appendectomy) የምንለዉ ዋነኛው ሕክምና ሲሆን መግል የያዘ ትርፍ አንጅት መጀመሪያ መግሉን በማስወገድ አልያም ፀረባክቴሪያ መድኃኒቶችን በመጠቀም የቀዶ ጥገና ጊዜው የሚራዘምበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡

 ቀዶ ጥገናው ከተደረገ በ12 ሰዓት ውስጥ እቅስቃሴ መጀመር ይችላል።

ምንጭ፡[email protected]ኢትዮጤና

 

  

Related Topics