ለጤናዎ - የጉልበት መጋጠሚያ እና የጡንቻ ጅማትዎን ደህንነት እንዲህ ይጠ

ለጤናዎ - የጉልበት መጋጠሚያ እና የጡንቻ ጅማትዎን ደህንነት እንዲህ ይጠብቁ

 

ሰውነት ለሚያደርገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ የእግር ሚና ከፍተኛ ነው።

ከእግርዎ ክፍል ደግሞ ሁሉንም ሰውነት መሸከም ያስችልዎት ዘንድ የሚረዳዎ ጉልበት ትልቁን ድርሻ ይወጣል።

በዚህ የሰውነት ክፍል ላይ የሚደርስ ጉዳት አደገኛና ምናልባትም መንቀሳቀስን ሊከለክልዎት የሚችል ነው።

በዚህ አካል ላይ መጋጠሚያ እና ጅማት አካባቢ የሚደርሱ ጉዳቶችን ቤት ውስጥ ይህን በማዘጋጀት መከላከል ይችላሉ።

የሚያስፈልጉ ነገሮች፦ 250 ሚሊ ሊትር ውሃ፣ 40 ግራም ለውዝ እና ማር ለየብቻ፣ 7 ግራም ቀረፋ፣ 2 ኩባያ የአናናስ ጭማቂ፣

1 ኩባያ አጃ፣ 1 ኩባያ የብርቱካን ጭማቂ፣

 አዘገጃጀት፦ መጀመሪያ አጃውን ብቻውን በደንብ ማብሰል።

 በንጹህ እቃ ውስጥ የብርቱካን ጭማቂውን መገልበጥ እና በደንብ ማዋሃድ።

ከዚያም አናናሱን፣ ቀረፋውን፣ ለውዙን እና ማሩን በመጨመር በደንብ ማቀላቀል።

የበሰለውን አጃ ከእሳት አውርዶ የተዘጋጀውን ውሃ ጨምሮ ማዋሃድ።

በመጨረሻም የቀረው ውህድ ላይ አጃውን ገልብጦ በደንብ አድርጎ መቀላቀል እና መጠቀም።

እነዚህ ውህዶች ሲልከን፣ ቪታሚን ሲ፣ ብሮሜሊየን እና ማግኒዥየምን በውስጣቸው የያዙ ናቸው።

ይህ ደግሞ ሰውነት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ማከም እና መከላከል ከማስቻሉም በላይ ለሰውነት ሃይልና ብርታትንም ይሰጣል።

እናም ይህን ቀላል ውህድ በማዘጋጀት እና በመጠቀም የጉልበትዎን ደህንነት ይጠብቁ።

 

source: FBC

 

  

Related Topics