የመንፈስ ጭንቀት መንስኤዎች፤ መፍትሄዎች

Depression

 

የመንፈስ ጭንቀት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለይ እንደ ሀዋሳ ባሉ ከተማ ነዋሪዎች የሚታይ ፈቃድ ያለው ችግር ነው፡፡ እንደ ዶ/ር ላውድሮ በአሜሪካ ሚኑሉታ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ እምነት የመንፈስ ጭንቀት የሚፈጠረው አዕምሮአችን ውስጥ በርካታ ነገሮች ለብቻ ለማብላላት በምናደርገው ጥረት ነው፡፡ አንድ ሰው በውስጡ የያዘውንና እርሱ ምላሽ ያጣውን ለብዙ ጊዜአት በአዕምሮ ውስጥ ይዞ መቆየት የመንፈስ ጭንቀት ይፈጥራል፡፡

 

መንፈስ ጭንቀት መንስኤዎች

 

ፍርሀት (መሰረት የሌለው የአዕምሮአዊ ስጋት)

በከተማችን ብዙዎች ከዚህ ስጋት ውስጥ ይብሰለሰላሉ፡፡ በዋነኛነት የሚጠቀሱት የጤና መታወክ ፍርት፣ ማንነትን የማጣት ፍርሀት፣ የውድቀት ፍርሀት፣ እርግጠኛ ያለመሆን እና የመሆን ፍርሀት……..ወዘተ

 

መገለል

ማህበረሰቡ ዘንድ በመልካቸው (አፍንጫው ደፍጣጣ፣አይኑ መንሸዋረር፣የጆሮ መጠን መተለቅ) አልያም በተፈጥሮ የተለያዩ አካላቸው ላይ ችግር ያለባቸው ወይም አንዳንድ እንከን ያለባቸው ሰዎች ለመንፈስ ጭንቀት ይጋለጣሉ፡፡

 

ፍላጎትን አለመግለፅ

ሰዎች በፍቅርም ይሁን በሌላ ፍላጎታቸውን ለመግነፅ ባለመቻላቸው የመንፈስ ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በወጣቶች ዘንድ የሚከሰተው የመንፈስ ጭንቀት ችግር ፍላጎታአውን ግልፅነትን ለመግለፅ ካለመቻል የሚመጣ ነው፡፡

 

የመንፈስ ጭንቀት ምን ያስከትላል

  • የመንፈስ ጭንቀት ከሚያስከትላቸው ከባባድ ችግሮች መካከል የመዘናጋት ባህሪይ ነው፡፡ መዘንጋት የሚባለው ፈጥኖ አንድ ነገር ለማስታወስ ያለመቻል ከጥቂት ሰዓታት በፊት ያሉትንና ያደረጉትን ያለማስታወስ ይህ ደግሞ በትምህርት ወቅት ከባድ ችግር ሊፈጥር የሚችል ነው፡፡

 

  • ከዚህ ቀደም የአዕምሮ ህመምተኞች ማገገሚያ በገቡ 100 ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት 70 ያህሉ ለ አዕምሮ ችግር የተጋለጡት የመንፈስ ጭንቀት ሰለባ ሆነው ከቆዩ በኃላ ነው፡፡

 

የመንፈስ ጭንቀት መፍትሄዎች

 

ለችግሩ በቀላሉ መፍትሄነት የሚመረጠው ለዚህ ህክምና የሚሰጡ ማለትም የምክር እገዛ የሚደርጉ ባለሙያዎች ጋር መሄድ ነው፡፡ ከነዚህ ባለሙያዎች ጋር በሚደረግ ውይይት ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ መልኩ መከላከል ካልተቻለ የአዕምሮ ምርመራ ወደሚደረግባቸው ሆስፒታሎች ማምራት ይመረጣል

 

ከደመላሽ ዱባለ

 

 

  

Related Topics